የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

Date:

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና የፋይናንስ ገበያን በዘላቂነት ለማቀላጠፍ ያለመ አዲስ አህጉራዊ የቦንድ ልውውጥ ፈንድ እስከ 250 ሚሊዮን ዶላር በሚደርስ ግዙፍ የገንዘብ ድጋፍ ተመስርቷል።

በታዋቂው ሊጋል ኤንድ ጀነራል ተቋም የሚተዳደረው ይህ አዲስ ፈንድ፤ በኤስ ኤንድ ፒ ዳው ጆንስ ኢንዴክሰስ እና በአፍሪካ ኤክስፖርት-ኢንፖርት ባንክ በተደገፈው የገንዘብ እና ዘላቂነት ተቋም በጋራ የተዘጋጀውን የቦንድ መለኪያ የሚከተል መሆኑ ተገልጿል።

ፈንዱ ተቋማዊ ባለሀብቶች በአፍሪካ የዶላር ኖት የተሰጡ የመንግሥት ቦንዶች ላይ ሰፋ ያለ እና የተለያየ የኢንቨስትመንት ዕድል እንዲያገኙ የሚያስችል ሰፊ በር ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።

የ ኤል ኤስ ኤፍ መስራች እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ቬራ ሶንግዌ ለጉዳዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

እርሳቸው እንዳሉት ከሆነ፣ የዚህ ፈንድ ዋና ዓላማ የአፍሪካን የብድር ሁለተኛ ገበያ ዕድገት እውን ማድረግ ነው።

የንግድ እንቅስቃሴውን የተሟላ የንግድ መጠን ለማድረስ ገበያው 1 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ወሳኝ ደረጃ ላይ መድረስ እንዳለበት ሶንግዌ አሳስበዋል።

ለአዲሱ ፈንድ ስኬት የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ እና ልማት ቢሮ የመነሻ ካፒታል ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...