የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ፖሊሲ በአዲስ ሊተካ ዝግጅት እየተደረገ ነው

Date:

አሁን በስራ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የውሃ_ፖሊሲ በ1992 የኢነርጂ ፖሊሲው ደግሞ በ1986 የወጣ ነው።

ይህ ከ20 ዓመት በላይ ሳይሻሻል መቆየቱ ፖሊሲው ወቅቱ የሚጠይቀውን ጥያቄ የመመለስ አቅም እንዳይኖረው አድርጎታል ተብሏል።

ኢትዮጵያ ካሏት 12 ተፋሰሶች 8ቱ ድንበር ተሻጋሪ መሆናቸውን ያነሱት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የውሃ ነገር ከመጠጥና የሃይል ምንጭነት ባለፈ የዲፕሎማሲ፣ የፀጥታና ቀጠናዊም ጉዳይ ነው ብለዋል።

ይህንን ሊመጥን የሚችል የጊዜውን ጥያቄ የሚመልስ ፖሊስ ማሰናዳትም የግድ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል። 

አሁን በስራ ላይ ያለው ፖሊሲ የድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን አጠቃቀም፣ የግድብ ደህንነትን በተመለከተና መሰል የውሃ አስተዳደር ጥያቄዎችን የመመለስ ክፍተት ያለበትና ነጥቦቹን በዝርዝር ያላፍታታ ነው ተብሏል።

የኢነርጂ ፖሊሲውም የግሉ ዘርፍ እንዲሳተፍ ያልተካተቱ ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችንም እንዲይዝ ተደርጎ ረቂቅ ፖሊሲው መሰናዳቱን አብራርተዋል።

የፖሊሲ ረቂቁ ትናንት የተወካዮች ምክር ቤት የውሃ መስኖና አየር ንብረት ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የተባሉ ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት ቀርቦ ተጨማሪ የማዳበሪያ ሀሳብ ተዋጥቶበታል።

ረቂቅ ፖሊሲው የሚጨመሩ ሀሳቦች ታክለውበት ወደ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ይላካል ተብሏል።

ከሸገር 102.1

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...