የኢዜማ ፖርቲ አዲሱ መሪ

Date:

አቶ ኢዮብ መሳፍንት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) መሪ የነበሩትን ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በመተካት የፓርቲው መሪ ሆነው ተመረጠዋል፡፡

ፓርቲው በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማኒፌስቶውን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በቀጣይ የሚመራበትን 50 ፖሊሲዎችንም ለአባላቱ ይፋ አድርጓል፡፡

ፖሊሲዎቹ በተለይም በሀገር መንግስት ግንባታ፣ በብሔራዊ ጥቅም፣ ልማትና ኢኮኖሚ እንዲሁም በአካታችነትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኢዜማ በአስቸኳይ ስብሰባው እዮብ መሳፍንትን የፓርቲው መሪ እንዲሁም ንጋቱ ወልዴን ምክትል መሪ በማድረግ የመረጠ ሲሆን፥ የቀድሞውን የፓርቲው መሪ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና ምክትላቸውን በክብር ሸኝቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመረጃ ነጻነት አዋጅን በሙሉ ድምፅ አጸደቀ

በምክር ቤቱ የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ እውነቱ...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...