የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

Date:

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ ፓርክ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች፣ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር እና ሌሎች አምባሳደሮች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት የሚሊተሪ አታሼዎች እና ጥቂት በሕይወት ያሉ ዘማቾች በተገኙበት ታስቧል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በዓሉን በማስመልከት በላኩት መልዕክት፣ “የኮሪያ ዘማቾች ጀግንነት ዛሬ ላለው መከላከያ ሠራዊት መሠረት በመሆኑ የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል” ብለዋል።

በኢትዮጵያ የኮሪያ አምባሳደር ጁንግ ካንግ በበኩላቸው የኮሪያ የዛሬ ዕድገት የተገነባው በከፍተኛ መሥዋዕትነት መሆኑን በማንሳት፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለከፈሉት የማይረሳ ውለታ ምስጋና አቅርበዋል።

አምባሳደሩ አክለውም የደቡብ ኮሪያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ጋር በተለያዩ የልማትና የትብብር መስኮች ያለውን ወዳጅነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የቃኘው ሻለቃ ለሰው ልጆች ነፃነት ሲል ባሕር አቋርጦ በመዝመት አንዲትም ወታደር በጠላት ሳይማረክበት ታሪክ ሠርቶ የተመለሰበትን ገድል የሚዘክር መጽሔትም የዝግጅቱ አንድ አካል ሆኖ ቀርቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...