“የወርቅ ምርት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ ነው”

Date:

የጋምቤላ ክልል ባለፉት ሰባት ወራት ከ4 ሺህ 488 ኪሎ ግራም በላይ የተጣራ ወርቅ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገቢ ማድረጉን አስታውቋል።

ይህም መጠን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1 ሺህ 175 ኪሎ ግራም ብልጫ ያለው ሲሆን፥ ክልሉ ካቀደው ግብም በላይ 988 ኪሎ ግራም ተጨማሪ ምርት ማስመዝገብ ችሏል።

ይህ ስኬት የተመዘገበው መንግስት በዘርፉ ላይ ባደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያና ጥብቅ የቁጥጥር ስራዎች መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም በዲማ፣ አቦቦ፣ ጋምቤላና መንጌሽ ወረዳዎች የሚገኙ ባህላዊ አምራቾችና ግዙፍ ኩባንያዎች ለውጤቱ መገኘት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ይህም ሀገሪቱ የያዘችውን የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ትግበራ ውጤታማ እያደረገው ይገኛል።

ክልሉ በቀጣይም የተቀናጀ የክትትልና የድጋፍ ስራዎችን በማጠናከር፣ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከ6 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ለማስገባት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የክልሉ ማዕድን ሀብት ልማት አመልክቷል።

ይህ ሂደት የክልሉን ማዕድን ለዓለም ገበያ በሕጋዊ መንገድ በማቅረብ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ግኝት እንደሚያሳድገው ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...