የዋጋ ግሽበትን ለመቋቋም የዜጎችን ገቢ ማሳደግ ላይ በትኩረት መሥራት ይገባል

Date:


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ትናንት በህዝብ ተወካዮች ምክር ተገኝተው ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሌላ በኩል የ2018 የፌደራል መንግሥት በጀት 1.93 ትሪሊዮን ብር ሆኖ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቋል።

ይህን አስመልክቶ ኢቲቪ በዳጉ ወቅታዊ ፕሮግራሙ የምጣኔ ሀብት ባለሙያው ቆስጠንጢኖስ በረኸ ተስፋን (ዶ/ር) ስቱዲዮ ጋብዞ አነጋግሯል።

ባለሙያው የዚህ ዓመት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ዕድገት 8.4 በመቶ መድረሱ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራው ያመጣው ለውጥ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህ አኃዝ ሀገሪቱ ያስመዘገበችውን ጥቅል የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያሳይ መሆኑን አንስተው፤ በግልም ሆነ በመንግሥት ደረጃ ለአበዳሪዎች የብድር ጥያቄ በሚቀርብበት ወቅት ለመፍቀድ ይህ አኃዝ ከግምት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ኢንቨስተሮችም ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሲፈልጉ ይህን አኃዝ የሚመለከቱ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዓለም ጦርነትን ጨምሮ በተለያዩ ተግዳሮቶች በምትፈተንበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ያስመዘገበችው ዕድገት አመርቂ መሆኑን ነው የተናገሩት።

የኢኮኖሚ ዕድገት ሲነሳ የዋጋ ንረት ጉዳይ አብሮ ይነሳል ያሉት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ፤ የዋጋ ግሽበት ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን አንስተዋል።

ይህን ለመቋቋም በመሰረታዊነት የዜጎችን ገቢ ማሳደግ ላይ በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ነው የጠቆሙት።

በዚህ ረገድ መንግሥት ከሚያከናውነው ሥራ ጎን ለጎን ግለሰቦችም ገቢያቸውን በማሳደግ ሕይወታቸውን ለማሻሻል የራሳቸውን ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው አመላክተዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...