ጄኔራል አልብሩሀን በርካታ የዩክሬይን ቅጥረኛ ወታደሮችን “መደምሰሳቸውን” አስታወቁ፡፡
በሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን የሚመራው የሱዳን ጦር ሀይል ባወጣው መግለጫ በዳርፉር ግዛት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የውጭ አገር ቅጥረኛ ወታደሮች መገደላቸውን ገለፀ፡፡
ከእነዚህ ውስጥ የዩክሬይን ወታደሮች እንደሚገኙበትም አስረድቷል፡፡
እንደመግለጫው የጦር ሀይሉ 6ተኛ ክፍለ ጦር በአልፈሽር ውስጥ በሚገኘው አል ካራማ የተሰኘ አደባባይ ላይ ባከናወነው ልዩ ዘመቻ የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል፡፡
በዚህም ለፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ተሰልፈው ሲዋጉ የነበሩ የውጭ አገር ወታደሮች የኪሳራው አካል መሆናቸውን አስታውቋል፡፡
እንደመግለጫው ከተገደሉት ውስጥ የዩክሬይንና የኮሎምቢያ ዜግነት ያላቸው ቅጥረኞች ይገኙበታል፡፡
በመግለጫው እነዚህ ቅጥረኛ ወታደሮች የድሮን ኦፐሬተርና የስናይፐር ተኳሽ በመሆን ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸውንም አስረድቷል።
