የሮማ ካቶሊክ ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ሊዮ 14ተኛ በጋዛ ምግብ እና እርዳታ እየጠበቁ ያሉ ዜጎች ላይ እስራኤል ጥቃት አድርሳለች፤ በርካታ ፍልስጤማውያንም ሕይወታቸው አልፏል ብለዋል።
ፖፕ ሊዮ አክለውም የዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብ በጋዛ እየደረሰ ያለውን ጭካኔያዊ ድርጊት እንዲቆም እጠይቃለሁ፣ ሰላም ሊሰፍን ይገባል ሲሉም አስምረውበታል።
እስራኤል በበኩሏ አሁንም በመሐል ጋዛ ያሉ ዜጎች በአስቸኳይ ስፍራውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ ሰጥታለች።
በተያያዘም ከራፋህ እና ከዴይር አል ባላህ ዜጎች እንዲወጡ እየተገደዱም ሲሆን፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ ይህ ትእዛዝ 85 ሺህ ሕዝቦችን የሚጎዳ ነው ብሏል።
ድርጅቱ ለአዲስ ተፈናቃዮች ሰብአዊ እርዳታን በማድረስ ዙርያም ከእስራኤል ባለሥልጣናት ጋር እየመከረበት እንደሆነ አስታውቋል።
