ለረጅም አመት የቡናማዎቹ ፕረዚዳንት የነበሩት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ቡናማዎቹ በይፋ ለቀዋል ።
ኢትዮጵያ ቡናን ከአርባ አመት በላይ በተለያዩ የስራ ቦታዎች የመሩት እና ላለፉት ሀያ አመታት የክለቡ ፕሬዝዳንት ሆነው ያገለገሉት መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ ከክለቡ ፕሬዝዳንትነት በይፋ ለቀዋል።
ከረጅም አመት በኋላ ጠቅላላ ጉባኤ እያደረገ የሚገኘው ክለቡ በጉባኤው ዶክተር እስራኤል ደገፉን አዲሱ ፕሬዝዳንት አድርጎም መርጧል።
ለቀጣይ 4 አመት ኢትዮጵያ ቡናን በቦርድ አባልነት የሚመሩ ተወካዮች የሚወከሉበት የቡና ሴክተር ይህን ይመስላል።
1, ከኢትዮጵያ ካፌ ኤክስፐርት አይሶሴሽን…..3
2,ከቡና አቅራቢዎች አቅራቢዎች……………..2
3,ከቡናና ሻይ ግብይት ባለስልጣን……………1
4,ከሀገር ውስጥ ቡና ጅምላ ባለስልጣን……1
5,ከኢትዮጵያ ቡናዎች ቆይዎች ማህበር……..1
6,ከኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ማህበር………..2
7,ከከፍተኛ ስፖንሰር አድራጊዎች…………….1
8,ከክብር አባላት..……………………………1
ከለቡን የሚመራው ፕሬዝዳንት ደግሞ የሚመረጠው “የኢትዮጵያ ካፌ ኤክስፐርት አይሶሴሽን” ከወከላቸው ሦስት ሰዎች ውስጥ ነበር ።
ዶክተር እስራኤል ደገፋ ፣አቶ አክሊሉ ካሳ እና አቶ ይስማሸዋ ሱዩም የመጨረሻ እጩዎች ሆኖ ቀረበው ነበር ።
