ጎተራ አካባቢ ሊፈርስ መሆኑ ተሰማ

Date:


በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኘውና ጎተራ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር ሊፈርስ መሆኑን ዘሪፖርተር እንግሊዘኛ ጋዜጣ ትናንት ባቀረበው ዘገባ አስታውቋል፡፡

‹‹አዲስ ቱሞሮው›› በሚል ፕሮጀክት የከተማው አስተዳደር ለሚያስገነባው ልዩ የኢኮኖሚ መንደር አካባቢውን ለማፍረስ መታቀዱንም አስረድቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ ከንነቲባ አዳነች አቤቤና በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የሚመራ እንደሆነ የጠቀሰው ዘገባው የከተማው አስተዳደር መንደሩን ለመገንባት ከቻይናው የኮሚኒኬሽንና ኮንትራክሽን ድርጅት ጋር ስምምነት መፈፀሙን አስታውቋል፡፡

መንደሩ የንግድ፣ የፋይናንስ፣ የትምህርት፣ የባህልና ሰማይ ጠቀስ የመኖሪያ ህንፃዎች እንደሚኖሩት መገለፁን ያስረዳው ዘገባው በመሆኑም በጎተራ አካባቢ በሚገኝ ሰፊ መሬት ላይ ለመስራት እንደታሰበ ጠቅሷል፡፡

የአዲስ ቱሞሮው መንደር ግንባታ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር እንደሚፈጅ አስረድቶም ከዚህም በላይ በጎተራ አካባቢ የሚኖሩ በርካቶችን እንዲፈናቀሉ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በኮሪደር ልማትና በጫካ ፕሮጀክት ፕሮጀክቶች አማካኝነት በመቶ ሺ የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተፈናቅለው ወደተለያዩ አካባቢዎች እንዲሰፍሩ የተደረገ ሲሆን በዚህኛው ፕሮጀክትም በርካታ ነዋሪዎች ተመሳሳይ እጣ እንደሚገጥማቸውም አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ ለሚገኘው ቅርንጫፉ ተጨማሪ 1.4 ቢሊዮን ሺሊንግ ኢንቨስት አደረገ

የኬንያው የቴሌኮም ግዙፍ ኩባንያ ሳፋሪኮም እስከ ሰኔ 2018 ዓ.ም...

በምክክሩ ሕዝበ ውሳኔ የተጠየቀባቸው ጉዳዮች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 15ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች በተጠናቀሩ...

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...