ፓኪስታን እስራኤልን በኒውክለር መሳሪያ ልትመታ ትችላለች ተባለ

Date:

እስራኤል ኢራንን በኒውክለር የምታጠቃ ከሆነ ፓኪስታን በተመሳሳይ በኒውክለር መሳሪያ በእስራኤል ላይ ጥቃት  እንደምታደረስ የኢስላሚክ አብዮታዊ ዘብ  ጄኔራልና የኢራን ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አባል ተናገሩ፡፡

ከፍተኛ የእስላሚክ አብዮታዊ ዘብ ጄኔራል እና የኢራን ብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት አባል ሞህሰን ረዛኢ ከኢራን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸዉ ቃለመጠይቅ፤ ‹እስራኤል እኛን በኒውክለር መሳሪያ የምታጠቃ ከሆነ ፓኪስታን የአጸፋ እርምጃ በኒውክለር መሳሪያ እንደምትወስድ ቃል ገብታልናለች› ብለዋል፡፡

የፓኪስታን ሻህን -3 የተሰኘዉ ሚሳኤል 2 ሺህ 7 መቶ ኪሎሜትር ተጉዞ በእስራኤል የትኛዉም ክፍል ላይ ጉዳት የማድረስ አቅም አለዉ ተብሏል፡፡

ጀነራሉ ይህን ቢሉም እስካሁን ግን በፓኪስታን ባለስልጣናት በኩል የተባለ ነገር የለም፡፡

ይሁን እና ፓኪስታን የእስራኤልን ጥቃት ተከትሎ ከኢራን ጎን መሰለፏን እየገለጸች ትገኛለች፡፡

የፓኪስታን የመከላከያ ሚኒስትር ካዋጃ አሲፍ ሰኔ 14 ቀን በብሔራዊ ምክር ቤት ንግግር ባደረጉበት ወቅት የሙስሊም ሀገራት በእስራኤል ላይ አንድ እንዲሆኑ ጥሪ ማቅረባቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

የእስራኤል ጥቃት ኢራንን ብቻ ሳይሆን የመንን እና ፍልስጤምን ጭምር ያነጣጠረ መሆኑንና አንድ አለመሆን ሁሉንም የሙስሊም ሀገራት ለተመሳሳይ ጥቃቶች ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው አስጠንቅቀዋል ታይምስ ኦፍ ኢዲያን እንደዘገባው ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...