ፕሬዚዳንት ፑቲን ወደ ቻይና

Date:


የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ቻይና ይጓዛሉ ተባለ። ፕሬዚዳንት ፑቲን ‘በሻን’ካይ’ ትብብር ድርጅት ጉባዔ (SCO) ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከሞስኮ ሚዲያዎች የሚወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና ምድር ለአራት ቀናት ያህል ይቆያሉ።

ከወዳጃቸው የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋርም በተለያዩ ዓለም አቀፍ እና የሁለቱ አገራት ግንኙነት ዙሪያ ላይ ለመምከርም ዕድሉን ይፈጥራሉ ቭላድሚር ፑቲን።

ፑቲን “በሻን’ካይ” ትብብር ጉባዔ ላይ ይሳተፋሉ የሚል መረጃም የወጣ ሲሆን፣ ከ2024 ወዲህ ረዘም ላለጊዜ ከአገር ውጪ ሲቆዩም ሆኖ ይመዘገብላቸዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን መቼ ወደ ቻይና ያቀናሉ ስለሚለው ቁርጥ ያለ ቀን ባይቀመጥለትም የኤስ ሲ ኦ ጉባዔ የሚጀምረው በፈረንጆቹ ነሐሴ 31 በመሆኑ ቀድውም ሊጓዙ ይችላሉ የሚል ዜናም በመውጣት ላይ ነው።

ከትብብሩ ጉባዔ ባሻገር ቤይጂንግ፣ ጃፓን በሁለተኛው የዓለም ጦርነት እጅ የሰጠችበትን 80ኛ ዓመት በፈረንጆቹ መስከረም 3 ታክብራለችና ፑቲንም መድረኩ ላይ ሊገኙ ይችላሉ የሚል ግምት ተቀምጡል።

ሩሲያ የሁለተኛውን ዓለም ጦርነት የድል በዓል ከቻይና ቀድማ ግንቦት ዘጠኝ ላይ ማክበርዋ ይታወቃል።

አር ቲ እንዳስነበበው

NBCEthiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...