ፖሊስ ከአዲስ ስታንዳርድ የወሰዳቸውን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በአፋጣኝ እንዲመልስ ሲፒጄ ጠየቀ

Date:

11 hours ago

በፖሊስ በተወሰዱት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል ስጋቱንም ገልጿል

ፖሊስ በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ባደረገው ብርበራ በወሰዳቸው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ውስጥ የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙ እና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ ሲል የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች የሆነው ተቋም (ሲፒጄ) ትላንት ሚያዚያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ስጋቱን አስታወቀ።

በአዲስ ስታንዳርድ ላይ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን ምርመራ እንዲያቋርጥ የጠየቀው ሲፒጄ፤ የተወሰዱት የተቋሙ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎችንም በአፋጣኝ እንዲመልስ አሳስቧል።

“አዲስ ስታንዳርድ ላይ የተፈጸመው ብርበራ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኢትዮጵያ መንግስት ነፃ ሚዲያዎችን ዝም ለማሰኘት እያካሄደው ያለው ዘመቻ አካል ነው፤ የተቋሙን የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች መውሰዱ በውስጣቸው የሚገኙ ከስራ ጋር የተያያዙና የግል መረጃዎች አላግባብ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችልበት እድል ከፍተኛ ነው” ሲሉ የሲፒጄ አፍሪካ ፕሮግራም አስተባባሪ ሙቶኪ ሙሞ ስጋታቸውን መግለጻቸውን አስታውቋል።

ስድስት የደንብ ልብስ ያልለበሱ የፖሊስ አባላት መሆናቸውን የገለጹ ሰዎች ሚያዝያ 9 ቀን2017 ዓ.ም የአዲስ ስታንዳርድን ቢሮ መበርበራቸውን፣ የዜና ክፍል ኃላፊውንና የሰው ሃብት አስተዳደር ሃላፊውን ለምርመራ ወደ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መውሰዳቸውን የድርጅቱ መስራች ፀዳለ ለማ ለጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ተቋሙ (CPJ) ተናግረዋል።

ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳላቸው ቢናገሩም፣ ግልባጭ ሳያሳዩ ወደ ተቋሙ ቢሮ ዘው ብለው መግባታቸውን፤ የተቋሙ ጋዜጠኞች ሁከት ሊያስከትል የሚችል ዘጋቢ ፊልም በማዘጋጀት ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ እንደነገሯቸው ፀዳለ ተናግረዋል፡፡

አክለውም፤ ክሱ ሀሰት መሆኑንና ድርጅቱ ዘጋቢ ፊልሞችን የማዘጋጀት አቅም እንደሌለው መግለጻቸውን ሲፒጄ በመግለጫው አካቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...