✞ ሥርዐተ ጸሎት ወስግደት ዘዓርብ (ስቅለት) ✞

Date:

✨✨✨ ዐርብ ነግህ /ጠዋት/፤ በ፲፪ት ሰዓት፤✨✨✨ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

አምላካችን በጥንተ ተፈጥሮ በፍጥረት መካተቻ ( በ6ኛው ቀን) በዕለተ ዓርብ አዳምን ፈጥሮታል፡፡ ዓርብ ከግእዙ ዐረበ ―ገባ፣ ተከተተ፣ ተጠናቀቀ ከሚለው ግሥ የወጣ በመሆኑ፤ ዐርብ ማለት መግቢያ፣ መካተቻ ማጠናቀቂያ ማለት ይሆናል። በሐዲስ ኪዳን የሥራም መካተቻ በመሆን ጌታችን በዚህ ዓለም በሥጋ ተገልጦ የሦስት ዓመት ከሦስት ወር ሥራውን ሠርቶ በዚህ ቀን የመጨረሻውን የመስቀል ሥራውን ሠርቶ አርፎበታልና ዐርብ ተብሏል። የስቅለት ዓርብ መልካሙ ዓርብም ይባላል። አዳምና ልጆቹ ለ5ሺህ 500 ዘመን ሲጠብቁት የነበረው የተስፋ ቃል ኪዳን የተፈጸመበትና የወንበዴዎቸ መቀጣጫ የነበረው መስቀልም የዲያብሎስ ድል መንሻ ከደዌ ሥጋና ከደዌ ነፍስ መፈወሻ ሆኖ የተሰጠበት በመሆኑ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ዕለት ከንጋት ጀምራ በጸሎት፣ በስግደት፣ በኅዘን፣ በለቅሶ፣ በመጨረሻም በሰርክ (11 ሰዓት) ንሴብሖ ለእግዚአብሔር እያለች በመዝሙር ፈጣሪዋን ታመሰግንበታለች።

በስቅለት ዓርብ በቤተክርስቲያን በቅድስቱ በስተምዕራብ የቤተ መቅደሱ በር ተዘግቶ፤ በቤተ መቅደሱ በር ፊት ለፊት ምንጣፍ ተነጥፎ፣ አልጋ (መሰል) ተዘጋጅቶ በአልጋው ላይ ምንጣፍና መጎናጸፊያ ለብሶ፣ በትራስጌውና በግርጌው የወርቅ ለምድ ተደርጎ፣ በላዩም ወንጌል ጽዋዎችና ጻሕሎች ተቀምጠው፤ በአልጋው አጠገብ በመቅደሱ ጎን ፫ት መስቀሎች ቆመው፤ ከመካከለኛው መስቀል በላይ ሥዕለ ስቅለቱ በላይ፤ እንዲሁም ሦስት ጽንሐዎችን ሰቅለው ገመድ ታስሮባቸው፣ የተለያዩ የቤተክርስቲያን ንዋያት (ዐውድ፣ ማሕፈዳት፣ ……. ) ወጥተው፣ የቤተክርስቲያን ዓምዶች በተለያዩ አልባሳት አጊጠውና መብራቶች በርተው እንዳበቁ፤ በካህኑ የአሥርቆት ጸሎት ካደረገ በኋላ አቡነ ዘበሰማያትና 41 ጊዜ ኪርዬ ኤሌይሶን ተብሎ ውዳሴ ማርያም ከተደገመ በኋላ ቀጥሎ ያለውን (በዓርብ በዜማ የሚዜሙት ጸሎቶች አብዛኞቹ በዕዝል ዜማ ነው የሚባሉት) በመሪና በተመሪ (መሪ ወገን እየቀደሙ ተመሪ እየተከተሉ) አንድ ጊዜ ይበሉ በመጨረሻ በግራና በቀኝ በኅብረት አንድ ጊዜ ይዝለቁ፡፡

█► አቡን ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፫) ነአምን ሕማሞ ለዘኢየሐምም ርግዝተ ገቦሁ ነአምን ወቅንዋተ እደዊሁ ነአምን ዬ ዬ ዬ ነአምን ሞቶ ወትንሣኤሁ፡፡

‹‹ለከ ኃይል››ን …… በል
█► ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም
█► አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም
█► ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለመ ዓለም
█► ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ እስመ ኮንከኒ ረዳእየ እብል በአኮቴት
አቡነ ዘበሰማያት /አባታችን ሆይ/
ከቻልን እየመላለስን ፲፪ ግዜ እያልን መስገድ ፲፪ ጊዜ ካልቻልን የቻልነውን ያህል ይህን ስንጨርስ በዛው ቀጥለን ፦
█► ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለማኅየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለምኩናኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም
█► ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ እስከ ለዓለም

የኦሪትና የነቢያት መጻሕፍት፤ ቀጥሎም ከተአምረ ማርያም ጀምሮ ሌሎች ተአምራትን (ተአምረ ጻድቃን፣ ተአምረ ሰማዕታት፣ ተአምረ መላእክት) እና ተአምረ ኢየሱስን ያንብቡ፡፡
ቀጥሎ ያለውን ምስባክ ከስግደት ጋር ዲያቆኑ እየመራ ሕዝቡ እየተመራ አንድ አንዴ ሁለት ጊዜ ከተባለ በኋላ፤ ሦስተኛውን በኅብረት ይበሉ፤
█► ምስባክ (መዝ.፳፮፥፲፪)፤

                   እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፤
                         ወሐሰት ርዕሰ ዐመፃ፤
                     እስመ ቆሙ ላዕሌየ ሰማዕተ ዐመፃ፡፡

(የክፋት ምስክሮች ተነሱብኝ፤ ክፋት የኃጢአት ራስ ናትና)
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ፤ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ፡፡

█► የማቴዎስ ወንጌል ፳፯፥፩-፲፬ ከተነበበ በኋላ፤
ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት፥ ይስቅልዎ ለኢየሱስ ዲበ ዕፀ መስቀል፡፡
█► የማርቆስ ወንጌል ፲፭፥፩-፭ ከተነበበ በኋላ፤
ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት፥ አውጽዕዎ አፍአ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ፡፡
█► የሉቃስ ወንጌል ፳፪፥፷፮-፸፩ ከተነበበ በኋላ፤
ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት፥ አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወመጠውዎ ለጲላጦስ፡፡
█► የዮሐንስ ወንጌል ፲፰፥፳፰-፵ ከተነበበ በኋላ፤
ወጸቢሖ ተማከሩ ሊቃነ ካህናት፥ አውጽዕዎ ለኢየሱስ ወነበረ ዐውደ ሶቤሃ፡፡
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ‹‹ኪርዬ ኤሌይሶን›› ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ፡፡ ከዚህ በኋላ የየሰዓቱን መልክአ ሕማማት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /የሰባቱ ጊዜያት ጸሎት፤ የእመቤታችን፣ የመድኃኔዓለምና የሥላሴ/ ያድርሱ።

       ✨✨✨    ዐርብ ጠዋት በሦስት ሰዓት    ✨✨✨
                   ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

█► አቡን ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፫) አርዑተ መስቀሉ ፆረ (፪) ይስቅልዎ ሖረ ዬ ዬ ዬ ከመኪያነ ይቤዙ እግዚኦ ኮነ ገብረ፡፡
‹‹ለከ ኃይል››ን …… በል
ከኦሪት እስከ ተዓምረ ኢየሱስ ያሉት ምንባባት ተነበው፤ ከወንጌል ምስባክ አስቀድሞ አንድ ካህንና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ በመልበስ፤ ካህኑ በሥዕለ ስቅለቱ ፊት በመቆም በመካከለኛው ጽንሐ ውስጥ ፍሕምና ዕጣን ጨምሮ ጽንሐው ላይ በታሰረው ገመድ እያወዛወዘ መዝሙረ ዳዊት ፴፬ን በ፫ት በመክፈል እንደሚከተለው ያድርሱ፤
በመጀመሪያ መዝ.‹፴፬፥፩-፪›ን (ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ) የሚለውን ይበል። ሕዝቡም ከስግደት ጋር እየተቀባበሉ ሦስት ጊዜ ይበሉ፤ ቀጥሎም ዲያቆኑ መዝ. ‹፴፬›ን (ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ እስከ ለነዳይ እምዕደ ዘይትኤገሎ ድረስ) በውርድ ንባብ ያንብብ፡፡
ይ.ካ (ይ.ሕ) ካህኑና ሕዝቡ፤
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ፤
ጽብኦሙ እግዚኦ ለእለ ይጸብኡኒ፤
ግፍኦሙ እግዚኦ ለእለ ይገፍኡኒ፤
ቀጥሎም ሁለተኛ ካህን እንደ መጀመሪያው ከሕዝቡ ጋር ግፍኦሙ የሚለውን ሦስቴ ይበሉ፤ ዲያቆኑ ‹‹ለነዳይ ወለምስኪን እምዕደ ዘይመስጦ›› ጀምሮ እስከ ‹‹ወኢይትፈስሑ ጸላዕትየ ላዕሌየ እለ ይጸልኡኒ በዐመፃ›› ድረስ) በውርድ ንባብ ያንብብ፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ ሦስተኛ ካህን እንደ መጀመሪያው ከሕዝቡ ጋር ግፍኦሙ የሚለውን ሦስቴ ይበሉ፤ ዲያቆኑ ከ‹‹እለ ይጻረሩኒ በከንቱ ወይትቃጸቡኒ በአዕይንቲሆሙ›› ጀምሮ እስከ መጨረሻው /ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም/ ድረስ) በውርድ ንባብ ያንብብ፡፡ ሕዝቡም አሜን በማለት ይቀበል፡፡
█► ምስባክ (መዝ.፳፩፥፲፮)፤

                          ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤
                       ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን፤
                          ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን፤

(ብዙ ውሾች ከበቡኝ፤ የክፋተኞች ጕባኤም በአንድነት ያዙኝ)
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ፤ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ፡፡

█► የማቴዎስ ወንጌል ፳፯፥፲፭-፲፮ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት፥ አኀዝዎ ለኢየሱስ ወወስድዎ ይሰቅልዎ፡፡
█► የማርቆስ ወንጌል ፲፭፥-፮-፲፭ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት፥ አሕየወ ሎሙ በርባንሃ ወወሀቦሙ ኢየሱስሀ ይስቅሉ፡፡
█► የሉቃስ ወንጌል ፳፫፥-፲፫-፳፭ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት፥ ወሰድዎ ለኢየሱስ ውስተ ዐውደ ምኵናን፡፡
█► የዮሐንስ ወንጌል ፲፱፥፩-፲፪ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ሠለስቱ ሰዓት፥ ቀሠፎ ጲላጦስ ለኢየሱስ ወመጠዎሙ ይስቅልዎ፡፡
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ‹‹ኪርዬ ኤሌይሶን›› ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ፡፡
ከዚህ በኋላ የየሰዓቱን መልክአ ሕማማት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያድርሱ፡፡

       ✨✨✨   ዐርብ ቀትር፤ በስድስት ሰዓት  ✨✨✨
                    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

█► አቡን ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፫) ተሰቅለ (፫) ወሐመ ቤዛ ኵሉ ኮነ ዬ ዬ ዬ በመስቀሉ ቤዘወነ እሞት ባልሐነ፡፡
‹‹ለከ ኃይል››ን …… በል
ከኦሪት እስከ ተዓምረ ኢየሱስ ያሉት ምንባባት ተነበው፤ ከወንጌል ምስባክ አስቀድሞ በ፫ ሰዐት እንደተደረገው ሥርዐቱን ያድርሱ፤ ዜማውን ካህኑና ሕዝቡ እየተቀባበሉ ፫ጊዜ ከስግደት ጋር በአራራይ ዜማ ያድርሱ፡፡
ይ.ካ (ይ.ሕ) ካህኑና ሕዝቡ፤
ለመስቀልከ ንሰግድ ኦ ሊቅነ፤
ወለትንሣኤከ ቅድስተ ንሴብሕ ኵልነ፤
ይእዜኒ ወዘልፈኒ፤
ቀጥሎ ዲያቆኑ በውርድ ንባብ በ፫ ከፍሎ የሚከተለውን ያንብብ፤ ሕዝቡም ‹‹ቅዱስ..›› የሚለውን የኪዳን ጸሎት ይበሉ፡፡
ይ.ዲ፤ ገላ. ፮፥ ፲፬-፲፯ ‹‹ኦ መኑ ዝንቱ በስድስቱ እለት ወበጊዜ ስድስቱ ሰዓት ተቀኖከ ዲበ ዕፀ መስቀል፤ …››
ይ.ሕ፤ ቅዱስ እግዚአብሔር፥ ቅ.ኃያል፥ ቅ.ሕያው ዘኢይመውት
ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፤ ቅ.እግዚአብሔር፥ ቅ. ኃያል፥ ቅ.ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ አግዚኦ፡፡
ቀጥሎ ዲያቆኑ በውርድ ንባብ ከግብረ ሕማማት በየመሐሉ ያንብብ፡፡

 ሦስት ካህናትና አንድ ዲያቆን ጥቁር ልብሰ ተክህኖ ለብሰው በሥዕለ ስቅለት ፊት ይቀመጡ፤ ከአንዲት መብራት በቀር ሌላውን ያጥፉና አንድ ግምጃ በራሳቸውና ገጻቸው ላይ ያድርጉ (ምዕመናን ደግሞ በነጠላቸው ይሸፈኑ)፤ አንገታቸውን ዝቅ አድርገው በዕዝል ዜማ በታላቅ ድምፅ በሐዘንና በፍርሃት በልቅሶና በዕንባ ጭምር ካህኑና ሕዝቡ በመቀባበል አምንስቲቲንና ተዘከረነ እግዚኦን እያንዳንዱን ሦስት ሦስት ጊዜ ይዝለቁ እስከ አራት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ 72 እስኪሞላ ይድገሙ)፤ እንደገናም አምንስቲቲንና ተዘከረነ እግዚኦን እያንዳንዱን አንድ አንዴ በመቀባበል በሁለት ዙር (አጠቃላይ ቊጥሩ 12 እስኪሞላ ይድገሙ)፡፡ ዲያቆኑም በየክፍሉ በሐዘን ዜማ በውርድ ንባብ እያስገባ ያንብብ፡፡
ይ.ካ (ይ.ሕ) ካህኑና ሕዝቡ፤
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ፤
አምንስቲቲ ሙዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ፤
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ፡፡
ይ.ካ (ይ.ሕ) ካህኑና ሕዝቡ፤
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፤
ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ፤
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ፡፡
ይ.ሕ(ሕዝብ)፤ በከመ ተዘከርኮ ለፈየታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ፡፡
█► ምስባክ (መዝ.፳፩፥፲፮)፤

                       ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ፤
                    ወኈለቊ ኵሎሙ አዕፅምትየ፤
                          ቀነዉኒ እደውየ ወእገርየ፡፡

(እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፤
አጥንቶቼንም ሁሉ ቈጠሩ)
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ፤ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ፡፡

█► የማቴዎስ ወንጌል ፳፯፥፳፯-፵፭ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ስድስቱቱ ሰዓት፥ አልበስዎ አልባሲሁ ለኢየሱስ ወወሰድዎ ይስቅልዎ፡፡
█► የማርቆስ ወንጌል ፲፭፥-፲፮-፴፫ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ስድስቱ ሰዓት፥ ቀትር ሶቤሃ ሊቃነ ካህናት ስቀልዎ ለኢየሱስ ማዕከለ ክልኤ ፈያት፡፡
█► የሉቃስ ወንጌል ፳፫፥-፳፯-፵፬ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ፮ቱ ሰዓት፥ዐበጥዎ ለስምዖን ከመ ይፁር መስቀሉ
█► የዮሐንስ ወንጌል ፲፱፥፲፫-፳፯ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ስድስቱ ሰዓት፥ ሰቀልዎ ለኢየሱስ በቀራንዮ መካን፡፡
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ‹‹ኪርዬ ኤሌይሶን›› ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ፡፡
 ከዚህ በኋላ የየሰዓቱን መልክአ ሕማማት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያድርሱ፡፡

        ✨✨✨    ዐርብ ተሰዓት፤ በዘጠኝ ሰዓት  ✨✨✨
                     ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

█► አቡን ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፫) ሶበ ሰቀልዎ (፫) ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ዬ ዬ ዬ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት፡፡
‹‹ለከ ኃይል››ን …… በል
 ከኦሪት እስከ ተዓምረ ኢየሱስ ያሉት ምንባባት ተነበው፤ ከወንጌል ምስባክ አስቀድሞ ካህኑና ሕዝቡ እየተቀባበሉ ሦስት ጊዜ ከስግደት ጋር ኦ ዘጥዕመ የሚለውን ይበሉ፡፡

ይ.ካ (ይ.ሕ) ካህኑና ሕዝቡ፤
ኦ ዘጥዕመ ሞተ በሥጋ (፫)

          █►        ምስባክ (መዝ.፷፰፥፳፩-፳፪)፤

                        ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
                         ወአስተዩኒ ብሒዐ ለጽምዕየ፤
                         ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፡፡

(በምግቤ ውስጥ ሐሞት ጨመሩበት፤
ለጥማቴም ሆምጣጤን አጠጡኝ)
ከአራቱም ወንጌል ካህኑ ካነበበ በኋላ፤ ቀጥሎ ያለውን ቃል ከስግደት ጋር በኅብረት ይበሉ፡፡
█► የማቴዎስ ወንጌል ፳፯፥፵፮-፶ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት፥ ጸርሐ ኢየሱስ በቃሉ ወይቤ ኤሎሄ ኤሎሄ፡፡፡፡
█► የማርቆስ ወንጌል ፲፭፥-፴፬-፴፯ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት፥ ገዓረ ኢየሱስ በቃሉ ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፡፡
█► የሉቃስ ወንጌል ፳፫፥-፵፭-፵፮ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት፥ ከልሐ ኢየሱስ በቃሉ ወአማኅጸነ ነፍሶ ሶቤሃ፡፡
█► የዮሐንስ ወንጌል ፲፱፥፳፰-፴ ከተነበበ በኋላ፤
ጊዜ ተስዓቱ ሰዓት፥ አጽነነ ርእሶ ኢየሱስ ወይቤ ተፈጸመ ኵሎ፡፡
ከዚህ በኋላ ተግሣጻትን የ‹‹ኪርዬ ኤሌይሶን›› ጸሎትና ስግደት እስከ ቡራኬ ድረስ ያድርሱ፡፡

 ከዚህ በኋላ የየሰዓቱን መልክአ ሕማማት ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ያድርሱ፡፡

      ✨✨✨ ዐርብ ሠርክ፤ በዐሥራ አንድ ሰዓት ✨✨✨
                    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

█► አቡን ፤
ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ (፫) ንዜኑ (፫) ዘአምላክነ ኂሩተ ትሕትና ወየውሀተ ዘእንበለ ዐቅም ዬ ዬ ዬ እንዘ ይጼዕልዎ ኢጸዐሎሙ ወኸእንዘ ያሐምምዎ ኢተቀየሙ፡፡
በዚህ ሰዓት የለከ ኃይል፣ የኪርዬ ኤሌይሶን ስግደት፣ የሠርክና የንዋም መልክአ ሕማማት የለም፤ የሰዓቱን ምንባባትም በቅዳሜ ሌሊት ማንበብ ይቻላል፡፡

ዐርብ ጠዋት ወጥተው የነበሩት ንዋያተ ቅድሳት ኹሉ ወደ ቦታቸው ከተመለሱ በኋላ ካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው ሥርዐተ ግንዘትን ይሥሩ፤ ፫ ካህናትም ሥርዐተ ግንዘቱን በእጃቸው አቅፈው ይያዙት፣ አንድ ካህን መስቀልና ጽንሐሕ ይዞ በኋላቸው ይከተል፣ አንድ ዲያቆን ደግሞ መስቀልና መብራት ይዞ ፊት ለፊት ይምራ፤ በምዕራብ በኩል ፊታቸውን ወደ ምሥራቅ አዙረው ይቁሙ፤ ከዚህ በኋላ በ፬ቱም ማዕዘናት እየዞሩ ፬፻ እግዚኦታ ያድርሱ አደራረሱም ካህናቱና ሕዝቡ በግራና በቀኝ በአራቱም አቅጣጫ በአራት ተመድበው በመቆም፤
በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ (4×5=20)፣
በንዑስ ዜማ ባለአምስቱን ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ (4x5x9=180)፣
እንደገና በዐቢይ ዜማ አምስት አምስት ጊዜ (4×5=20)፣
በንዑስ ዜማ በእንተ ማርያም ዘጠኝ ዘጠኝ ጊዜ (4x5x9=180)
ምሕላው ከተፈጸመ በኋላ ካህኑ አቡነ ዘበሰማያት ይስጥ፤ እስከ ትንሣኤ ድረስ የኑዛዜ ጸሎት ስለሌለ ካህኑ ፵፩ ጊዜ ኪርዬ ኤሌይሶን ይበል፤ ሕዝቡም እንደርሱ ይጸልዩ፡፡

ከዚህ በኋላ በቅኔ ማሕሌት ኹሉም ይሰብሰብ፣ መቋሚያ ይዘው፣ በመካከላቸው መብራት (ጧፍ) አብርተው ይያዙ፣ የዳዊትንና የነቢያትን ጸሎት ከሕዝቡ ጋር እየተቀባበሉ ያንብቡ፤ እነዚህም የሚከተሉት ናቸው፤
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ንኡስ አነ እምአኃውየ፤መዝ.፻፶(፻፶፩)፥፩-፰
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ እግዚኦ ኢትጸመመኒ፤መዝ.፻፰፥፩
ይ.ሕ.፤ ለይሁዳ ወልዱ ወለውሉደ ውሉዱ ይደምሰስ፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ኄር፤መዝ.፻፴፭፥፩
ይ.ሕ.፤ እስመ ለዓለም ምሕረቱ፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ይባርክዎ ኵሉ ግብረ እግዚእ፤መዝ.ሠለ.ደቂቅ ፩
ይ.ሕ.፤ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር፤ጸሎተ ሙሴ ፩
ይ.ሕ.፤ ስቡሐ ዘተሰብሐ፡፡
ይ.ዲ(ይ.ካ)፤ ፍካሬ ዘጻድቃን ወዘኃጥአን፤መዝ.፩፥፩ ይ.ሕ.፤ ከአንባቢው ጋር ያስተዛዝሉ።

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ አንድን አንብበው መጨረሻው ላይ ‹‹ወፍኖቶሙሰ ለኃጥአን ትጠፍእ›› ሲባል፤ በመካከላቸው የየዙትን መብራት (ጧፍ) በመቋሚያ መትተው ያጥፉት፡፡ ከዚህ በኋላ መዘምራኑ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር እንደ ሥርዐቱ ይዘምሩ፡፡
ካህናቱ ሕዝቡን በወይራ ቅጠል እየጠበጠቡና ስግደት እያዘዙ ወደቤታቸው ይሸኟቸው፡፡

    ▬▬▬▬▬▬   ✞✞✞ ✞✞✞ ✞✞✞ ▬▬▬▬▬▬

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃማ ወድካም ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሣኤሁ እግዚአብሔር በፍስሓ ወበሰላም አሜን !!!
ያለ ደዌና ያለ ሕማም ያለጥምና ያለ ድካም እግዚአብሔር ለትንሣኤው ብርሃን እንደ ዛሬ ቀን በደስታና በፍቅር በአንድነት ያድርሰኝ ያድርሳችሁ አሜን !!!
✨✨✨✨✨ ✞ ✨ ✞ ✨ ✞ ✨✨✨✨✨

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫ በሚያካሂድባቸው ቦታዎች ሁሉ እሳተፋለሁ

በዘንድሮው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ...

በሲዳማ ክልል ከ62% በመቶ በላይ የሚታረሰው መሬት በአሲዳማነት የተጎዳ ነዉ

በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ የሚታየው የምርታማነት ማነቆ በዋናነት የመሬት አሲዳማነት...

የኢትዮጵያ እዳ እና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎች ስብሰባ ሳይገኙ ቀሩ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ እዳ እና...

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት

የኢትዮጵያ እና ሕንድ የቆየ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት የአፍሪካ-ሕንድ...