ሀማስ ያልተቀበለው ውሳኔ

Date:


የአውሮፓ ህብረት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የጋዛን ግጭት ለማስቆም ያሳለፈውን ውሳኔ እንደተቀበለው አስታወቀ ።

የጋዛን ግጭት እስከወዲያኛው ይፈታል ተብሎ የታመነበትን ባለ20 ነጥብ የሰላም ዕቅድ ለቀጣናው አጠቃላይ ገፅታ አስፈላጊ መሆኑን ህብረቱ ገልጿል ።

የአውሮፓ ህብረት ቃል አቀባይ አኑዋር ኤል አኖኒ በብራሰልስ በሰጡት መግለጫ ፣ የተመድ ውሳኔ ሰብዓዊ እርዳታ በሚገባበት ፣የመልሶ ግንባታ በሚካሄድበት እና ተቋማዊ እድሳት በሚከናወንበት ሁኔታ መምከሩ እና ውሳኔ ላይ መድረሱ ትልቅ እርምጃ ነው ሲሉ አወድሰውታል ።

ህብረቱ ከተመድ እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመሆን በጋዛ አስተማማኝ ሰላም እንዲኖር ይሰራል ብለዋል ቃል አቀባዩ ።

ምን እንኳ የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ የሰላም እና ደህንነት አስከባሪ ሀይሎች እንደሚገቡ ከውሳኔ ቢደርስም ሀማስ ግን ውሳኔውን አልተቀበለውም ተብሏል ።

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...