በኢትዮጵያ ቤተመንግስት አስተዳደር ስር የሚተዳደሩት ድሬዳዋ ቤተ መንግስት እና የጅማ ግቤ አዳራሽ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል የሚያደርጋቸው ግንባታ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መድረሱን አራዳ ከኢትዮጵያ ቤተ መንግስት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ኩምሳ ሰምቷል።
የድሬዳዋ ቤተመንግስት የሆቴል ግንባታው ከሦስት ዓመታት በፊት ተጀምሮ አሁን ወደ መጠናቀቂያው ምዕራፍ ላይ ደርሷል ተብሏል።
በጅማ የሚገኘው ግቤ አራዳሽ የሆቴሉ ግንባታ በሸራተን አዲስ ሆቴል ድርጅት የተከናወነ ሲሆን፣፥ ሸራተን ኢንቨስት ያደረገበትን ሆቴል ለሦስት ዓመታት ወጪውን ለመተካት ከተገለገለበት በኋላ ለቦታው የኪራይ ክፍያ ለመንግስት መፈፀም እንደሚጀምር ተመላክቷል።
በሁለቱም ቤተመንግስቶች ቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ የኢትዮጵያ ንጉስ ሳሉ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ቤቶች የቅርስ ይዘታቸው ሳይነካ ተጨማሪ ግንባታዎችን በማከል ለአገልግሎት ዝግጁ እየተደረጉ መሆኑን ነው ዋና ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
