ለመምህራን ሆስፒታል ግንባታ 40 ሚሊዮን ብር ተሰበሰበ

Date:

የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር የተቋረጠውን የመምህራን ሆስፒታል ግንባታ መልሶ ለማስጀመር 40 ሚሊዮን ብር ማሰባሰብ መቻሉን አስታወቀ፡፡

የማህበሩ ፕሬዚዳንት መምህር ድንቅአለም ቶሎሳ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፤ የተማሪ ወላጆችን በማስተባበር የተቋረጠውን የመምህራን ሆስፒታል ግንባታ መልሶ ማስጀመር የሚያስችል 40 ሚሊዮን ብር አሰባስቧል፡፡

ባለፉት አራት ዓመታት ማህበሩ ለማከናወን ካቀዳቸው ተግባራት አንዱ የመምህራን ሆስፒታል ግንባታ እንደነበር አስታውሰው፤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተገኘ የቦታና ድጋፍ ግንባታው ተጀምሮ ነበር፡፡ ሆኖም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ግንባታው ተቋርጦ የሀብት ምንጭ በማፈላለግ ሂደት ላይ እንደቆዩ ገልፀዋል፡፡

“የሀብት ምንጮች አንዱ ያደረግነው የተማሪ ወላጆችን ነው” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ በዚህም ለመንግሥት ትምህርት ቤት ወላጆች 50 ብርና ከዚያ በላይ የሚሸጡ ደረሰኞችን፤ ለግል ትምህርት ቤት ተማሪ ወላጆች ደግሞ 100 ብርና ከዚያ በላይ የሚሸጡ ደረሰኞችን በማሰራጨት 40 ሚሊዮን ብር ማሰባሰባቸውን አስረድተዋል፡፡

ከተማሪ ወላጆች የምንጠብቀው እስከ 100 ሚሊዮን ብር ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ከዚህ ጎን ለጎን ሌሎች የገቢ አማራጮች እየታዩ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

የተሰበሰበው ብር ከዚህ በፊት ተቋርጦ የነበረውን ግንባታ ድጋሚ ማስጀመር የሚያስችል መሆኑንም ጠቁመው፤ በቀጣይነት ግንባታው ሳይቋረጥ እንዲከናወን ለማስቻል ከተለያዩ ባንኮች ጋር ብድር ለማመቻቸት እየተወያዩ እንደሚገኙም ገልፀዋል፡፡

በ2009 ዓ.ም ከከተማው አስተዳደር የተገኘውን አዋሬ አካባቢ የሚገኝ ሶስት ሺህ 600 ካሬ ቦታና 50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማስተባበር 2014 ላይ ዲዛይኑን አስጨርሰው ግንባታውን መጀመሩን ፕሬዚዳንቱ ከዚህ በፊት ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ ገልፀው እንደነበር ይታወሳል።

ጋዜጣ+

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...