ከጥር 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ቦታዎች ተሽከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የኮሪደር ልማትና የመንገድ ግንባታ በሚደረግባቸው ፦
- ከቅዱስ ኡራኤል፣ በአትላስ ሆቴል ኤድሞል እስከ ቦሌ ብራስ ድረስ፣
- አደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ
የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በመንገድ ስራው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደሩ መሆኑን ገልጿል።
ከጥር 04/2018 ዓ/ም ጀምሮ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑት ተሽከርካሪዎች በስተቀር ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሽከርካሪን አቁሞ መሄድ ፈፅሞ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።
