ለ19 ሀገራት ዜጎች የተሰጡ የግሪን ካርዶችን ክለሳ እንደምታደርግ አሜሪካ አስታውቃለች

Date:

ዩናይትድ ስቴትስ በዋሽንግተን ዲሲ በብሔራዊ ጥበቃ አባላቶቿ ላይ ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ ከተፈጸመው ጥቃት በኋላ፣ አስር የአፍሪካ ሀገራትን ጨምሮ ለ19 ሀገራት ዜጎች የተሰጡ የግሪን ካርዶችን አጠቃላይ ክለሳ እንደምታደርግ አስታውቃለች፤ ከእነዚህም መካከል ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ይገኙበታል ተብሏል።

የትራምፕ አስተዳደር ይህን እርምጃ መወሰዱን ያረጋገጠው ባለሥልጣናቱ ለጥቁቱ ተጠርጣሪ የሆነው ከዚህ ቀደም በአፍጋኒስታን ከአሜሪካ ኃይሎች ጋር ይሠራ የነበረ የ29 ዓመት አፍጋናዊ ዜጋ መሆኑን ከለዩ በኋላ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የዜግነት እና ኢሚግሬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር ጆሴፍ ኤድሎው በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሉት ፕሬዝዳንት ትራምፕ “ከአሳሳቢ ሀገር ለመጣ እያንዳንዱ የውጭ ዜጋ የተሰጠውን የግሪን ካርድ ዳግም ጥብቅ ግምገማ” እንዲደረግበት አዘዋል።

አክለውም አሜሪካውያንን መጠበቅ “ቅድሚያ የሚሰጠው” ጉዳይ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

በዚህ መመሪያ መሠረት፣ የሀገሪቱ ዜግነት እና ኢሚግሬሽን አገልግሎት አሁን ከተዘረዘሩት ሀገራት የግሪን ካርድ ማመልከቻዎችን ሲያስተናግድ “አሳሳቢ፣ አገር-ተኮር የሆኑ ነገሮችን” ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል።

ፖሊሲው ገና ውሳኔ ያልተሰጣቸው ማመልከቻዎችን እንዲሁም ከኖቬምበር 27 ቀን 2025 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ወይም ከዚያ በኋላ የቀረቡትንም ይመለከታል የተባለ ሲሆን፣ ይህም ለኢሚግሬሽን ሰራተኞች ውሳኔዎችን ለማዘግየት፣ ተጨማሪ ማስረጃ ለመጠየቅ ወይም ፈቃድ ለመከልከል ሰፊ ውሳኔ የመስጠት ስልጣን እንደሚሰጣቸው ተጠቁሟል።

በዚህ ፖሊሲ አሳሳቢ ተብለው ከተካተቱ ሀገራት መካከል አፍጋኒስታን፣ ምያንማር፣ ቻድ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኤርትራ፣ ሃይቲ፣ ኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ የመን፣ ቡሩንዲ፣ ኩባ፣ ላኦስ፣ ሴራሊዮን፣ ቶጎ፣ ቱርክሜኒስታን እና ቬንዙዌላ ይገኙበታል።

ተንታኞች እንደሚሉት ውሳኔው ዩናይትድ ስቴትስ ለሚሰለጥኑ ሠራተኞች፣ ለተማሪዎች እና ለስደተኞች ቁልፍ መዳረሻ በሆነችው አፍሪካ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል።

ኤርትራ፣ ሶማሊያ እና ሱዳን ቀደም ሲልም ጥብቅ የኢሚግሬሽን ቁጥጥሮች ይገጥሟቸው እንደነበር የተገለፀ ሲሆን ክለሳው ለዜጎቻቸው እክሎችን ይበልጥ ሊያጠናክር እንደሚችል ተመላክቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...