ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድርን ልታስተናግድ ነው

Date:

​ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድርን በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት የሚያስችላትን ዕድል ማግኘቷን የከተማዋ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ይፋ አደረጉ።

በዓለም አትሌቲክስ የውድድር ካላንደር ውስጥ በይፋ የተካተተውና “One Day Meeting” የተሰኘው ይህ ታላቅ ውድድር፣ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሚያዝያ 18 ቀን 2026 በአዲስ አበባ የሚከናወን ይሆናል።

​ከንቲባዋ ይህንን ታሪካዊ ድል አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት፤ ስኬቱ በከተማዋ ሲከናወኑ የቆዩ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች፣ የስፖርት ዲፕሎማሲ እና የመሠረተ ልማት መስፋፋት ሥራዎች ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።

የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ዋና ዳይሬክተር ፒርስ ኦክላጋን በኢትዮጵያ ባደረጉት ጉብኝት አገሪቱ ያላትን በቂ የማዘጋጀት አቅም መመስከራቸውን ተከትሎ የተመዘገበው ይህ ስኬት፣ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ታምኖበታል።

​በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የሚመራው ይህ ውድድር ለአገር ውስጥ ሙያተኞች የልምድ ልውውጥ ከመፍጠሩ ባለፈ፣ ለሚሳተፉ አትሌቶችም ከፍተኛ ሽልማት የሚያበረክት ነው።

ከንቲባዋ ለዚህ ውጤት መመዝገብ የላቀ ሚና ለተጫወቱት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ውድድሩ ኢትዮጵያ የአትሌቲክስ መገኛነቷን ለዓለም የምታሳይበትና የስፖርት ዲፕሎማሲዋን ወደ ላቀ ከፍታ የምታደርስበት መድረክ እንደሚሆንም ይጠበቃል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በሱዳን ብሉ ናይል ግዛት ብቻ ከ12ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አሉ

በሱዳን የሚገኘው የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ...

ትራምፕ አሜሪካ እና ኢራን “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት ውስጥ” ሊወያዩ እንደሚችሉ ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል “በሚቀጥሉት ሁለት ቀናት...

የኢራን ጦርነት የሚቀጥል ከሆነ የዓለም ምጣኔ ኃብት አደጋ ላይ እንደሚወድቅ አይኤምኤፍ አስጠነቀቀ

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) በመካከለኛው ምሥራቅ የሚካሄደው የኢራን...

የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የ፵ ቀን መታሰቢያ ጥሪ

​"የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው!" (ምሳሌ ፲፥፯)​በሕይወትና በቃል ትምህርታቸው ብዙዎችን...