ኢሰመኮ መንግሥት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበ

Date:

​በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በንጹሃን ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግድያ፣ እገታና መፈናቀል በአሳሳቢ ሁኔታ መቀጠሉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በተለይም ከጥቅምት 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በሽርካ፣ በጉና፣ በመርቲ እና በሌሎች የአርሲ ዞን አካባቢዎች የታጠቁ ኃይሎች በሰነዘሩት ተደጋጋሚ ጥቃት ሳቢያ የሰው ሕይወት መጥፋቱን፣ የአካል ጉዳት መድረሱንና መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመት መከሰቱን ገልጿል።

የግጭቱ መባባስ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችን ለስደት የዳረገ ሲሆን፣ የካቲት 19 ቀን በሽርካ እና ሮቤ ወረዳዎች በንጹሃን ላይ የተፈጸመው ግድያና እገታ የችግሩን አስከፊነት አጉልቶ አሳይቷል።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ መንግሥት የዜጎችን ደህንነት የማስከበር ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታውን እንዲወጣና በአካባቢው በቂ የጸጥታ ኃይል እንዲያሰማራ ጥሪ አቅርበዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...