መንግስት ለአፍሪካ ኅብረት ስብሰባ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ እንግዶችን በሃገሪቱ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጋብዟል

Date:

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፌስቡክ ገጽ ለኢንቨስተሮች የሚከተለው መልእክት ተላልፏል።
“በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳችን አማካኝነት፣ ግልጽ በሆነ የቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ፣ በዘመናዊ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጠናዎች፣ እንዲሁም ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና እና ለዓለም አቀፍ ገበያዎች ምቹ በሆነ ተደራሽነት ላይ የተመሠረተ፣ ለባለሀብቶች ቅድሚያ የሚሰጥ ምህዳር ገንብተናል።

“በስትራቴጂካዊና በዘላቂነት ላይ ባተኮረ አመራር የሚመራውና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚታገዘው የሀገራችን የኢነርጂ አቅርቦት 98% እና ከዚያ በላይ ታዳሽ ሲሆን፤ እየተስፋፋ ያለው ዲጂታል መሰረተ ልማት፣ የተሻሻለው የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት እና የሰለጠነ የሰው ኃይል በግብርና ቴክኖሎጂ (agritech)፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ በኢ-ኮሜርስ፣ በማዕድን እና በሌሎችም ዘርፎች ዘላቂ ትርፍ ለማስመዝገብ ዝግጁ ናቸው። ይህም ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በማጠናከር የአፍሪካን የጋራ ብልጽግና ያሳድጋል።”

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...