የግዢና ሽያጭ ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።
ሚድሮክ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ እንደሚያድሰውና ኢትዮጵያ ለምታዘጋጀው 32ኛውን የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንደሚያደርሰው ተናግሯል።
አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትውልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
