ምሁራን የባህር በር ጥያቄ ሲያነሱ መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ፤ ሂዱና ተዋጉ ይባሉ ነበር”

Date:

  • ሌፍተናንት ፈረደ አየለ

የኢትዮጵያ ምሁራን የባህር በር ጥያቄ በሚያነሱበት ወቅት “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ሂዱና ተዋጉ” ይባሉ ነበር ሲሉ ሌፍተናንት ፈረደ አየለ ገለጹ።

የቀድሞው የባህር ኃይል ባልደረባ ሌፍተናንት ፈረደ አየለ፣ ከጋዜጣ ፕላስ ቮድካስት ጋር በነራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ስለ ባህር ወደብ እንዳይወራ እና እንዳይነገር ተደርጎ ቆይቷል።

ማንኛውም ትውልድ ምሁር የተባለ ስለ ባህር ወደብ እንዳያነሳ መደረጉን ገልጸው፤ ደፍረው የሚያነሱና የሚናገሩትም በደህንነት ተይዘው እስር ቤት ይገቡ እንደነበርና ከስራቸው እንደሚባረሩ አስታውሰዋል።

የኢትዮጵያ ምሁራንም የባህር በር ጥያቄ በሚያነሱበት ወቅት “መንገዱን ጨርቅ ያድርግላችሁ ሂዱና ተዋጉ” እየተባለ ይሳቅባቸው እንደነበር ተናግረዋል።

በወቅቱ የነበሩት ባለስልጣናት ከስልጣናቸው እስኪወርዱ ድረስ ህዝቡን አሸማቀው ሰለወደብ እንዳይነገር በማድረግ ጉዳዩን አፍነውት ቆይተዋል ብለዋል።

በዚህም የኢትዮጵያ ትውልድ ስለ ባህር በር እና ባህር ማወቅና መጠየቅ የጀመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ መሆኑን አስታውቀዋል።

ጋዜጣ_ፕላስ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...