ምክር ቤቱ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ነገ ያፀድቃል

Date:

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያካሂደው አስቸኳይ ስብሰባው የተሻሻለውን የፌዴራል የገቢ ግብር ረቂቅ አዋጅን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል ።

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በዕለቱ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችንም ያጸድቃል።

የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር አዋጅ ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅም የእለቱ አጀንዳ ነው።

እንዲሁም የስታርታፕ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ
ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን እንደሚያጸድቅም ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በመንገድ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ...

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...