ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ተወያይተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት፤ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ዛሬ የኢዩቤልዩ ቤተ መንግሥትን መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሀገር ግንባታ ተገቢውን አስተዋጽኦ እንድታበረክት መንግሥት የሚጠበቅበትን ሁሉ እንደሚወጣም አመልክተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ለተመደቡት ብፁዓን አባቶች መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
