አርሰናል ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን ደረሰዉ
በሻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ሊቨርፑል ጋላታሳራይን 4ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፏ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅለዋል ። የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ስቦዝላይ ፣ ኤኪቲኬ ፣ ግራቨንበርች እና ሞሀመድ ሳላህ አስቆጥረዋል።
ባየር ሙኒክ አታላንታን በሀሪ ኬን ሁለት ፤ ካርል እና ሉዊስ ዲያዝ ግቦች 4ለ1 አሸንፏል። ባየር ሙኒክ በድምር ውጤት 10ለ2 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።
ቶተንሀም አትሌቲኮ ማድሪድን 3ለ2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። አትሌቲኮ ማድሪድ በድምር ውጤት 7ለ5 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፈዋል።
ባርሴሎና ኒውካስልን 7ለ2 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። ባርሴሎናን አሸናፊ ያደረጉ ግቦች ሌዋንዶውስኪ ሁለት ፤ ራፊንሀ ፤ ላሚን ያማል ፤ በርናል እና ፌርሚን አስቆጥረዋል።
የኒውካስል ዩናይትድን ግቦች አንቶኒ ኢላንግ በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል። ባርሴሎና በድምር ውጤት 8ለ3 በማሸነፍ ሩብ ፍፄሜውን ተቀላቅሏል።
የሩብ ጨዋታዎች ፒኤስጂ ከ ሊቨርፑል ፣ ማድሪድ ከ ባየር ሙኒክ ፣ ባርሴሎና ከ አትሌቲኮ ማድሪድ እና አርሰናል ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን ይግናኛሉ።
