ሪያል ማድሪድ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ

Date:

ሪያል ማድሪድ ከሪያል ኦቬዶ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ የሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሎስ ብላንኮዎቹን የማሸነፊያ ግቦች ኪሊያን ምባፔ 2x እና ቪንሰስ ጁኒየር ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ በሁለት የላሊጋ ጨዋታዎች ሶስተኛ ግቡን አስቆጥሯል።

ቪንሰስ ጁኒየር ተቀይሮ ወደ ሜዳ በመግባት አንድ ግብ ሲያስቆጥር አንድ አመቻችቶ አቀብሏል።

ሪያል ማድሪድ የመጀመሪያ ሁለት የላሊጋ ጨዋታዎችን ግብ ሳይቆጠርበት ሲያሸንፍ ከአስር አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር

⏩ ቅዳሜ – ሪያል ማድሪድ ከ ማዮርካ
⏩ ቅዳሜ – ሪያል ኦቬዶ ከ ሪያል ሶሴዳድ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport  

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ካናዳ ምዝገባም ሆነ ስምሪት አልተጀመረም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መቀመጫውን ካናዳ ካደረገው "ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል"...

የክቡር ዶክተር ጋሽ መሐሙድ አዲስ አልበም ለአድማጮች ሊደርስ ነዉ

ታዋቂው ድምፃዊ ክቡር ዶክተር አርቲስት መሐሙድ አሕመድ «ለታሪክ» የተሰኘውንና...

ሜታ ‘ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በቀረበባቸው ክስ 18 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ

ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ ኩባንያ ሜታ በፌስቡክ እና በኢንስታግራም ምክንያት...