RIDE በAfrica’s Best Brands Award ላይ Most Admired Ethiopian Brand በመሆን ለከፍተኛ ሽልማት በቅቷል::
በአዲስ አበባ United Nations Economic Commission for Africa (ECA) በተደረገው የሽልማት ስነ-ስርዓት ላይ ድርጅቱ ይህንን ታላቅ ክብርና ሽልማት በማግኘቱ የተሰማውን ደስታ ለመላው የራይድ ቤተሰብ ገልጿል።
ድርጅቱ በ2006 ዓ.ም “RIDE” የተሰኘውን የንግድ ስም እና ምልክት በኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ጥበቃ በማስመዝገብ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን የኤሌክትሮኒክ ታክሲ አገልግሎት ዘርፍ ፈር – ቀዳጅ ሲሆን በአሁን ወቅት በስፋት አገልግሎቱን እያቀረበ ይገኛል:: በተጨማሪም በFood Delivery እና ተዛማች አገልግሎቶች ላይ በመሪነት እያገለገለ ይገኛል::
ድርጅቱ እንዳለው “ይህንን ትልቅ ብራንድ ስንገነባ በነበረው ሂደት ከጎናችን ለነበራችሁ አሽከርካሪዎች ÷ ደንበኞቻችን እና መላው የራይድ ቤተሰቦች በቀጣይም ከኢትዮጵያ አልፎ በአፍሪካ በምናደርገው ጉዞ አብራችሁን በዘላቂ ወዳጅነት እንደምትቀጥሉ እንተማመናለን ብሏል።
