ለ7ኛ ጠቅላላ ምርጫ የተመዘገቡት ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች እነማን ናቸው?

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከናወነውን የመራጮች ምዝገባ ዝርዝር መረጃ ይፋ ያደረገ አድርጓል።

በጥቅሉ 54 ሚሊዮን 57 ሺህ 861 መራጮች መመዝገባቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገልጸዋል።

ይህ ሰፊ ቁጥር እነማንን ያካተተ እንደሆነ እና በምን ዓይነት ሁኔታ እንደተመዘገቡ ቦርዱ በዝርዝር አብራርቷል።

ምርጫ ቦርድ በመጀመሪያው ዙር ይፋ ካደረገው አጠቃላይ 50.5 ሚሊዮን ተመዝጋቢዎች መካከል አብዛኛውን ቁጥር የያዙት ሴቶች ናቸው። ቁጥራቸውም 27 ሚሊዮን 390 ሺህ 729 ደርሷል፤ ወንዶች ደግሞ 23 ሚሊዮን 123 ሺህ 426 ሆነው ተመዝግበዋል።

በዚሁ የመጀመሪያ ዙር ይፋ ከተደረጉት መካከል በምዝገባ ዘዴ ረገድ ሲታይ፣ 45 ሚሊዮን 10 ሺህ 594 መራጮች በማኑዋል የተመዘገቡ ናቸው፤ ቀሪዎቹ 5 ሚሊዮን 503 ሺህ 561 መራጮች ደግሞ ዘመናዊውን የዲጂታል ዘዴ ተጠቅመው የተመዘገቡ መሆናቸውን ቦርዱ አመልክቷል።

በፀጥታ ስጋት ምክንያት በመደበኛው ጊዜ ሳይመዘገቡ ቆይተው በኋላ ላይ ቦርዱ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመምከር ባመቻቸው ልዩ የጊዜ ሰሌዳ በ40 የምርጫ ክልሎች የተመዘገቡ 3 ሚሊዮን 368 ሺህ 454 መራጮችም የዚህ አጠቃላይ ቁጥር አካል ናቸው።

ከዚህ ባለፈም ቦርዱ ባደራጃቸው ልዩ የምርጫ ጣቢያዎች አማካኝነት 20 ሺህ 122 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዲጂታል ሲስተም የተመዘገቡ መሆናቸውን ሰብሳቢዋ ጠቅሰዋል።

28 ሺህ 632 የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች እና 126 ሺህ 498 የወታደራዊ ካምፕ አባላትም ተካትተው ምዝገባው መጠናቀቁ ተገልጿል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...