መጋቢት 30 በተጠናቀቀው የኩባንያው በጀት ዓመት 15.9 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ ማግኘቱን ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲመሳከር የ130 በመቶ ብለጫ አንዳለው የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄሌፑት አስረድተዋል፡፡
በጊዜው ኩባንያው 39.5 ቢሊዮን የኬንያ ሽልንግ ወይም 47.7 ቢሊዮን ብር አካከባቢ ኪሳራ አስመዝግቧል፡፡
ኪሳራው አምና በተመሳሳይ ጊዜ ከተመዘገበው በግማሽ ያህል መቀነሱንም ዋና ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል፡፡
ኩባንያው በዓመቱ ውስጥ ካገኘው 15.9 ቢሊዮን ብር ውስጥ 9.6 ቢሊዮን ብር ወይም ከ67 በመቶ በላይ ገቢው የተገኘው ከሞባይል ዳታ ሲሆን፣ 3 ቢሊዮን ብር ወይም 20 በመቶው ደግሞ ከድምጽ የተገኘ ገቢ መሆኑን ዋና ስራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡
የኩባንያው ገቢ ያደገው በዋናነት በቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር መጨመር፣ በሞባይል ዳታ አገልግሎቶች ላይ በተፈጠረ ከፍተኛ ፍላጎት እና የኤምፔሳ ዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር በመጨመሩ ነው ተብሏል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመላ ሀገሪቱ በአጠቃላይ 3500 የኔትወርክ ማማዎች አሉኝ፣ ከዚህ ውስጥ ከግማሽ በለዩ በራሴ የገነባኋቸው ነው ብሏል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም 1400 ማማዎች ላይ ኔትወርክ መዘርጋቱን የተናገረው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለዚህም በየዓመቱ ከ5 እስከ 6 ቢሊዮን ብር ለኪራይ አንደሚከፍል ዋና ስራ አስፈጻሚው ዊም ቫንሄሌፑት አስረድተዋል፡፡
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ3 ወራት ንቁ ደንበኞች ቁጥር 13.6 ሚሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ54.2 በመቶ እድገት አሳይቷል።
የኤምፔሳ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከእጥፍ በላይ በመጨመር 5.2 ሚሊዮን ደርሷል፣ በኤምፔሳ መተግበሪያ የተደረገው የገንዘብ ዝውውርም 32.5 ቢሊየን ብር ደርሷል ተብሏል፡፡
ኩባንያው ከመላው የሀገሪቱ ህዝብ 59.2 በመቶ የሚሆነውን የ4G ኔትወርክ ተጠቃሚ ማድረግ ችያለሁ ብሏል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፉት 5 ዓመታት በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 2.6 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስት ማድረጉን ተናግሯል፡፡
ይህ ኢንቨስትመንት ለኔትወርክ ማስፋፊያ፣ ለስራ ፈጠራ እና ቀጣይነት ያላቸውን ዕቅዶችን ለማሳካት ይውላል ብሏል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከባለፈው ዓመት የ130 በመቶ ብልጫ አተረፈ
Date:
