በዕውቀቱ በታላቁ ዓለም አቀፍ ፌስቲቫል ላይ ተመረጠ

Date:

ዝነኛው ደራሲና ገጣሚ በዕውቀቱ ሥዩም በስፔን ባርሴሎና በሚካሄደው 41ኛው ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል ላይ ግጥሞቹን  እንዲያቀርብ  ተጋብዟል።

ይህ ታላቅ ፌስቲቫል ከግንቦት 6 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆይ ሲሆን፣ በዕውቀቱ ግንቦት 13 ቀን በታሪካዊውና እጅግ ውብ በሆነው ‘ፓላው ዴ ላ ሙዚካ ካታላና’ አዳራሽ በሚካሄደው የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ግጥሞቹን ለዓለም ያሰማል።

ገጣሚው በዚህ መድረክ ከተለያዩ አህጉራት ከተመረጡ 7 ታዋቂ ገጣሚዎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፋዊ ለዛ በዓለም መድረክ ላይ ያስመሰክራል።

የባርሴሎና ዓለም አቀፍ የግጥም ፌስቲቫል እ.ኤ.አ ከ1985 ጀምሮ በየዓመቱ የሚካሄድና በዓለም ላይ ካሉ ጥንታዊና ዝነኛ የግጥም መድረኮች አንዱ ነው።

ፌስቲቫሉ በካታሎኒያ ባህል ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን፣ ግጥም ከሙዚቃ፣ ከዕይታ ጥበብና ከቪዲዮ ጋር ተቀናጅቶ የሚቀርብበት ልዩ ጥበባዊ ድግስ ነው።

በዕውቀቱ ሥዩም የግጥም ስራዎቹን የሚያቀርብበት ‘ፓላው ዴ ላ ሙዚካ ካታላና’ በራሱ በዩኔስኮ  የዓለም ቅርስነት የተመዘገበ አስደናቂ ሕንፃ ሲሆን፣ እንዲህ ባለው ታሪካዊ ቦታ ላይ የኢትዮጵያ ዜማ መሰማቱ የጥበብ ድንበር ተሻጋሪነትን ያሳያል።

ይህ ዝግጅት የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ ከዓለም አቀፍ አዝማሚያዎች ጋር የሚያስተሳስር ከመሆኑም በላይ፣ በዕውቀቱ በሳቅና በቁም ነገር የታጀቡ ግጥሞቹን ለዓለም በማካፈል የአገራችንን ገጽታ በበጎ ጎኑ የሚያስተዋውቅበት ታላቅ አጋጣሚ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምግባረ-መልካሙ ኢትዮጵያዊ

ስለሺ መንገሻ - ከ1934 እስከ 2018 ዓ.ም ሠሎሞን ለማ ገመቹ. ግዮን...

ትራምፕ ለኔታንያሁ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ...

ኤምባሲዎችና የውጭ ባለሀብቶች በ«ፍራንኮ-ቫሉታ» ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና የውጭ...

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ከዓመታዊ የትርፍ 90 በመቶውን እንዲያከፋፍሉ ሊደረግ ነው

የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ተብለው የሚቋቋሙ ፈንዶች ከዓመት ትርፋቸው ቢያንስ...