ጠረኑ ተረፈ ምርት ሲቀቀል የሚፈጠር ሲሆን ይህንም የሚያሥቀሩ ማሽኖች ብልሽት ሲገጥማቸው የሚከሰት እንደሆነ የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አታክልቲ ገ/ሚካኤል ተናግረዋል፡፡
ማሽኖቹን በአዲስ በመተካት፣ ሽታውን በዘላቂነት ለማስወገድ እየተሰራ ነው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
በቅርቡ 65 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገባቸው ለተረፈ ምርት የሚሆኑ ማሽኖችን አስገብተናል ያሉ ሲሆን አሁንም የሚመጡ አሉ ብለዋል፡፡
ይህ መጥፎ ጠረን በአካባቢው የሚስተዋለው የመሳሪያዎች ብለሽት ሲያጋጥም አልፎ አልፎ ነው እንጂ ሁሌ አይደለም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
(አራዳ ኤፍ ኤም)
