የኮሜዲያን እና ደራሲ ወንድወሰን አውራሪስ ሥርዓተ ቀብር ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።
በድንገተኛ የልብ ሕመም ምክንያት ህዳር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ሕይወቱ ያለፈው ኮሜዲያን እና ደራሲ ወንድወሰን፥ በበርካታ የኮሜዲ ሥራዎቹ፣ ፊልሞቹ፣ የመድረክ ቴአትር እና የሬዲዮ ፕሮግራም ይታወሳል።
በመተወን ብቻ ሳይሆን በድርሰትም የላቀ ተሰጥኦ እንደነበረው የሚነገርለት የጥበብ ሰው በቀብር ሥነ ስርዓቱ ላይ ቤተሰቦቹ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎቹ ተገኝተዋል።
በ49 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው ኮሜዲያን ወንድወሰን አውራሪስ ባለትዳር እና የአንድ ሴት ልጅ አባትም ነበር።
