ጦርነቱን ተከትሎ የኢትዮጵያውን ዜጎችን ደህንነት በተመለከተ አሐዱ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉም ጠይቋል፡፡ በቀጠናው ውጥረቱ ቢጨምርም እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያዊያን ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በምላሹ ለአሐዱ አስታውቋል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሰዎች ዝውውር መከላከልና የተመላሽ ዜጎች ድጋፍና ክትትል መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ደረጄ ተግይበሉ በመካከለኛው ምስራቅ ቀጠና ጦርነቱ ቢቀጥልም፣ በኢትዮጵያዊያን እና ትውልድ ኢትዮጵያዊያን ላይ የደረሰ ምንም ጉዳት አለመኖሩን ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም ስጋት ከሆነ ከሌሎች ሃገራት ጋር በመነጋገር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ በመርከብ ትራንስፖርት ጭምር ወደ ሃገራቸው ለማምጣት መንግስት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ በኩል ሃላፊነት ስላለበት ዝግጁ እንደሚሆን ለአሐዱ አስታውቀዋል፡፡
በቀጠናው እየተካሄደ ያለውን ውጥረት መንግስት በዜጎቹ ላይ አደጋ እንዳይደርስ በኢምባሴውች በኩል ጥብቅ ክትትል እያደረገ ነው ሲሉ የገለፁት አቶ ደረጄ፣ በዚህም አንድም ኢትዮጵያዊያን በስጋት መልክ እርዳታ እንዲደረግላቸው እስካሁን የጠየቁ አለመኖራቸውንም ገልፀዋል።
በተጨማሪ መንግስት በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥ መንገድና በተለያዩ መንገዶች ከሃገር የወጡ ዜጎችን ለመመለስ በሳምንት ሶስት ጊዜ በረራ በመመደብ 3ሺህ ዜጎችን በየሳምንቱ ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህንን የትራንስፖርት ወጭም የኢትዮጵያ መንግስት ከለጋሽ ሀገሮች ጋር በመሆን እየሸፈነ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሜሪካን ጨምሮ በምካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሃገራት ጋር ጥሩ የሆነ ድፕሎማሲያዊ ግንኙነት አላት የሚሉት አቶ ደረጄ ፣ በዚህም በዜጎቿ ደህንነት ጉዳይ ላይ በችግር ወቅት አስተማማኝ ጥበቃ እንዲያገኙ እድል ፈጥሮላታል ሲሉ ገልፀዋል።
