በማይናማር ርዕደ መሬት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል

Date:

በማይናማር በተከሰተው ርዕደ መሬትለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ ማለፉ ተሰምቷል።

በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 7 የተለካው ርዕደ መሬት ከማይናማር አልፎ በጎረቤተ ሀገራት ከባድ ንዝረት ማስከተሉን እና በአካባቢው ሀገራት መለስተኛ ጉዳት ማደረሱም ነው የተገለጸው።

የሀገሪቱ ሁለተኛ ትልቅ ከተማ የሆነችው ማንዳላይ ከባዱን ጉዳት ማስመዝገቧንከስፍራው የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች አሁንም ሰዎችን ከፍርስራሾች በህይወት ለማውጣት ጥረት እያደረጉ ይገኛል።

በታይላንድ መዲና ባንኮክበተከሰተ ሌላ ርዕደ መሬት በግንባታ ያለና ያላለቀ ህንጻ ተደርምሶ እስካሁን የሥድስት ሰራተኞች አስከሬን ሲገኝ ከ100 በላይ የሚሆኑት ሰራተኞች ደግሞ አልተገኙም ተብሏል።

በአደጋው እስካሁን 1 ሺህ ሁለት ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ 2 ሺህ 376 ሰዎችደግሞ መጎዳታቸውን የተገኙ የሆስፒታል ምንጮችን ዋቢ ያደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።

በፖለቲካዊ አለመረጋጋት ሳቢያ በተለይም በምዕራባውያን ማዕቀብ የተጣለበት የማይማናር ወታደራዊ አስተዳደር አሁን ላይ ዓለም አቀፍ እርዳታ እንዲደረግለት እየጠየቀ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...