በሮማንያ እሁድ እለት በተካሄደ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሊበራሊስት የሆኑት ኒኩሶር ዳን አሸንፈዋል።
የአውሮፓ ህብረት ደጋፊ ናቸው የሚባልላቸው ኒኩሶር ዳን ከተፎካካሪያቸው ጆርጅ ሲሞን የተሻለ ድምፅ በማግኘት ነው ምርጫው ያሸነፉት፡፡
በፕሬዚዳንታዊ ምርጫው ኒኩሶር ዳን አጠቃላይ ከተሰጠው ድምፅ 54 በመቶውን አግኝተዋል፡፡
ተፎካካሪያቸው ጆርጅ ሲሞን በበኩላቸው ከተሰጠው አጠቃላይ ድምፅ 46 በመቶ ማግኘታቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።
