የእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በጋዛ ላሉ ፍልስጤማውያን ምግብና መድኃኒትን ጨምሮ ሰብዓዊ ዕርዳታ በአስቸኳይ እንዲጀመር ትናንትና ፈቅደዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በአሜሪካ መንግሥት ጫና መሆኑ የተዘገበ ሲሆን፤ ከካቢኔያቸው አብላጫዎቹ ውሳኔውን እንደተቃወሙት ዘ ታይምስ ኦፍ እስራኤል ዘግቧል፡፡
በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዕርዳታ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን የእስራኤል ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለኢየሩሳሌም ፖስት ተናግረዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራምና የተባበሩት አረብ ኤሚርቶች ከዕርዳታ አቅራቢዎቹ ቀዳሚዎቹ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡
