በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ወታደራዊ ኃይሎች በመከላከያ ሠራዊት ሥር መዋሃዳቸውን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሙርሃፍ አቡ ቃስራ ገለጹ።
ሂደቱ ሁሉንም የሀገሪቱን ወታደራዊ ኃይሎች በአንድ ተቋማዊ ማዕቀፍ ሥር ለማዋቀር የተደረገው ሥራ ውጤት መሆኑ ነው የተገለጸው።
አቡ ቃስራ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ “ከተቋማዊ ሥራ አስፈላጊነት አንፃር፣ የተቀሩት ወታደራዊ ቡድኖችም ይህ መግለጫ በወጣ በ10 ቀናት ውስጥ አንዲቀላቀሉን እናሳስባለን” ብለዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም በዚህ ትዕዛዝ ላይ የሚዘገይ ወይም ውሳነውን የማይቀበል ማንኛውም ዓይነት ወታደራዊ ቡድን ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድበት አሳስበዋል።
ትዕዛዙ የመጣው በጥር ወር መገባደጃ ላይ አሳድን ከሥልጣን ያስወገዱት ኃይሎች ቁልፍ መሪ አህመድ አል ሻራ መሪነት በተደረገው ስብሰባ የሶሪያ ወታደራዊ ኃይሎች በመከላከያ ሚኒስቴር ሥር ለማድረግ ከተስማሙ በኋላ መሆኑን አናዶሉ ዘግቧል።
