“የደካሞች ብዝበዛ እንዲቆም፤ እንድንዋደድ እና አንድ እንድንሆን ያስፈልጋል”፦ ሊዮ 14ኛ

Date:

የአዲሱ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ካርዲናል ሮበርት ፕሪቮስት በዓለ ሲመት በቅዱስ ፔጥሮስ አደባባይ ተካሂዷል።

በ100 ሺህ የሚቆጠሩ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በዓለ ሲመት ላይ የቅዳሴ እና የፀሎት ሥነ-ሥርዓት ተደርጓል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት ሊዮ 14ኛ፥ የደካሞች ብዝበዛ እንዲቆም፤ እንድንዋደድ እና አንድ እንድንሆን ያስፈልጋል፤ ፈጣሪም የሚሻው እርሱን ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በካቶሊክ እምነት ውስጥ ‘የኃይማኖት ፕሮፖጋንዳ’ ቦታ እንደሌለው ጠቅሰው፤ መከፋፈል እና ፖለቲካዊ ጫና ከእምነት ውስጥ ሊወገዱ የሚገባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።

አያይዘውም፥ የምድርን የተፈጥሮ ሃብት ብሎም ደካሞችን የሚበዘብዝ የኢኮኖሚ ሥርዓት መገታት እንዳለበት ገልፀዋል።

በንግግራቸው መጨረሻ ለዩክሬን ዘላቂ ሰላም ተመኝተው፤ በጋዛ ወዳጅ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ ወገኖችን በፀሎት አስበዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የአሜሪካ ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ፣ የፔሩ ፕሬዚዳንት ዲና ቦሉዋርቴ እና የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪን ጨምሮ ከ150 በላይ የሀገራት ተወካዮች ተገኝተዋል።

ኢቢሲ ቴሌግራምን ይቀላቀሉ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...