✍️ በሴቶች 800 ሜትር አትሌት ጽጌ ዱጉማ ምርጥ ሰአት በማስመዝገብ አሸንፋለች። ርቀቱን ለማጠናቀቅ 1 ደቂቃ 56.64 ሰከንድ ወስዶባታል።
✍️ በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት በሪሁ አረጋዊ አሸንፏል፡፡ ርቀቱን በ12 ደቂቃ 50 ሰከንድ አጠናቋል።
አትሌት ኩማ ግርማ እና አትሌት መዝገቡ ስሜ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡
የ2025 ዳይመንድ ሊግ በቻይና ዢያመን ከተማ መጀመሩ ይታወሳል።
