በባንግላዲሽ የአየር ኃይል ጄት አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት አለፈ

Date:

በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ የአየር ኃይል ማሰልጠኛ ጄት አውሮፕላን ተከስክሶ ቢያንስ 19 ሰዎች ሲሞቱ 164 ሰዎች ቆስለዋል።

አደጋው የደረሰው የF-7 BGI የተሰኘ የአየር ሀይል ጄት ለልምምድ በተነሳ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በዳካ በሚገኝ ትምህርት  ቤት ጊቢ  የተከሰከሰ ሲሆን ቢያንስ 19 ሰዎች ለሞት ተዳርገዋል ።

ከሟቾቹ መካከልም የአውሮፕላኑ አብራሪ እና በርካታ ተማሪዎች ይገኙበታል  የተባለው ሲሆን በአደጋው ሰለባ የሆኑ ተማሪዎች

እድሜያቸው ከአራት እስከ 18 ዓመት መካከል እንደሆነ ተገልጿል ።

የአየር ኃይል ጀቱ ሚልስተን ኮሌጅ እና  ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ሲለሰከስ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ውስጥ እንደነበሩ ተዘግቧል።

ከባንግላዲሽ አየር ኃይል ኩርሚቶላ ቤዝ ከተነሳ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ባጋጠመው  የቴክኒክ ችግር ምክንያት አውሮፕላኑ ሊከሰከስ እንደቻለ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሌተና ኮሎኔል ሳሚ ኡድ ዶውላ ቾውዱሪ ተናግረዋል። ዘገባው የሮይተርስ ነው

NBC Ethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...