በኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት ስር የሚንቀሳቀሱ 29 ተቋማት እንዳሉም መረጃዎች ያሣያሉ ተቋማቶቹ በሚያወጡት የግዢ ጨረታ በከተማው የሚገኙ ነጋዴዎች ተሳታፊ መሆን ይጠበቅባቸዋል ፡፡
የአዲስ ቻምበር ተጠባባቂ ዋና ፀሐፊ አቶ ዘካሪያስ አሰፋ በሴሚናሩ ላይ እንደገለጹት የተባበሩት መንግስታት በሚያወጣቸው የአገልግሎትና የእቃዎች ግዢና ጨረታ የአዲስ አበባ ከተማ የንግድ ህብረተሰብ ይበልጥ ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆን ቻምበሩ እየሰራ ይገኛል ፡፡
የንግዱ ሕብረተሰብም ተወዳዳሪ እንዲሆን የአቅም ግንባታ ስራዎች ንግድ ምክር ቤቱ ከተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ያከናወናል ብለዋል።
ቻምበሩ በኮሚሽኑም ሆነ በሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች የሚወጡ የግዢ ፍላጎቶች የንግዱ ህብረተሰብ ተሳታፊና አቅራቢ የሚሆንበትን ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል ፡፡
