በትግራይ ክልል የወርቅ ማዕድን ፍለጋ ዕድሎችና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ቅዳሜ ሰኔ 27/ 2018 ዓ.ም በመቐለ በተካሄደው አውደ ጥናት፣ የ25 ዓመት የስትራቴጂ ፍኖተ ካርታ ያቀረቡት ፕሮፌሰር ምሩፅ ሓጎስ ፣ በ2015 እስከ 2017 ዓ.ም ባሉት ዓመታት 35 ቶን ወርቅ መመረቱን ገልጸዋል።
በቴክኖሎጂና በሙያ ማነስ ምክንያት 53 ቶን ወርቅ ለብክነት መዳረጉን ጠቁመው፣ ይህም ዘርፉ የሚገኝበትን ከፍተኛ ፈተና እንደሚያሳይ አስረድተዋል።
ፕሮፌሰሩ እንዳሉት፣ በማዕድን ፍለጋ የፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረገድ በፌደራልና በክልል መንግሥታት መካከል ያለው የስልጣን ክፍተት ዘርፉ በሚገባ እንዳያድግና እንዳይለማ አድርጎታል።
በቀጣዮቹ 25 ዓመታት ዘርፉን ለማሳደግ በፌደራል ስር ከሚገኙ አንዳንድ ስልጣኖችና ተግባራት ለክልላዊ መንግሥታት ሊሰጡ እንደሚገባ ሐሳብ አቅርበዋል።
በተጨማሪም የማዕድን ዘርፉን ለማጠናከር ግልጽና የተቀናጀ ፖሊሲና ስትራቴጂ መኖር፣ ያሉትን አዋጆችና ደንቦች ማሻሻል፣ የተረጋጋ የፖለቲካና የኢንቨስትመንት ሁኔታ መፍጠር እንዲሁም በቂ በጀት መመደብ እንደ ዋና ዋና የመፍትሔ ሐሳቦች ቀርበዋል።
@tikvahethiopia
