“ሹም ተምቤን” የተሰኘ አዲስ ፓርቲ በምስረታ ሂደት ላይ ነው
በትግራይ የሚንቀሳቀስ “ሹም ተምቤን” የተሠኘ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ የቅድመ ምዝገባ ፍቃድ በማግኘት በምስረታ ሂደት ላይ መኾኑን ዋዜማ ዘግባለች፡፡
ፓርቲው ከቦርዱ የምስረታ ፍቃድ ያገኘው ሐምሌ 23 ቀን 2017 ዓ.ም እንደነበር ተመላክቷል፡፡
ከእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን የተነጠሉ ግለሰቦች ያቋቋሙት “ውድብ ወለዶ ትግራይ” ወይም የትግራይ ትውልድ የተሰኘ የፖለቲካ ፓርቲም፣ መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ባካሄደው ጉባኤ በይፋ እንደተመሠረተ ይታወሳል።
በእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተቋቋመው ስምረት ፓርቲ በበኩሉ፣ በትላንትናው ዕለት፣ከመሥራቾቹ አንዱ የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳን የፓርቲው ሊቀመንበር አድርጎ መምረጡ ተዘግቧል፡፡
