በአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ላይ ሊተገብር ስለታሰበዉ …

Date:

ልጆቻቸውን ከ25 በላይ በሚሆኑ አለምአቀፍ ት/ቤቶች የሚያስተምሩ ወላጆች እና ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው ወገኖች በስራ አመራር ማሰልጠኛ ማእከል አዳራሽ መጋቢት 8/2018 ዓ.ም ተገናኝተው ባደረጉት ምክክር ሚኒስቴሩ በቅርቡ ባወጣው መመሪያ የአለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች የሀገሪቱን ብሔራዊ ስርአተ ትምህርት እንዲከተሉ እና የ70 /30 አሰራር ማለትም 70 በመቶ ኢትዮጵያውያን፣ 30 በመቶ የውጪ ሀገር ዜጎችን እንዲያስተምሩ የወጣውን መመሪያ ጥቅምና ጉዳቱ ላይ በዝርዝር መክረዋል።

ሚኒስቴሩ መመሪያውን ከማውጣቱ አስቀድሞ መመሪያው ያለው ፋይዳ በሚመለከት ተገቢውን ጥናት አለማድረጉ፣ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት አለማሳተፉ እንዲሁም መመሪያው ዜጎች ጥራት ያለው ትምህርት የማግኘት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን የሚጥስ ስለመሆኑ ዝርዝር ማብራሪያ በወላጅ ተወካዮች ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል።

በተጨማሪ 70/30 የሚለው ከየት የመጣ መስፈርት ነው? ለምን 20/80 ወይም 40/60….አልሆነም? መነሻው ምንድነው የሚለው በተጨባጭ እንደማይታወቅ ተነስቷል።

ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች የሀገራቸው ባህልና ታሪክ አውቀው መማር እንዳለባቸው የያዘው አቋም ሙሉ በሙሉ አንቃወምም ያሉት ወላጆች ግን ይኸን ለመተግበር ስርአተ ትምህርቱ ወደመቀየር መኬዱ የልጆቻችንም የእኛንም ሞራል የሚነካ፤ ወላጆች የተሻለ ትምህርት ልጆቻቸው እንዲያገኙ የነበራቸውን ህልም የሚያጨናግፍ ነው ብለውታል።

ወላጆች ውድ ዋጋ ከፍለው፣ ልጆቻቸውን ወደአለምአቀፍ ት/ቤቶች የሚልኩት በየትኛው ሀገር ተወዳዳሪ የሆነ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ካላቸው ህልም በመነሳት ነው። ይኸ ደግሞ ለሀገር የሚሰጠው ጥቅም የላቀ መሆኑን በሁሉም ወገኖች ዘንድ ግንዛቤ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የአለምአቀፍ ት/ቤቶች ተደራሽነት ከአንድ በመቶ በታች መሆኑን፣ ይኸን አነስተኛ ድርሻ እንዲያውም ማጠናከር ሲገባ የማጥፋት አካኼድ እኛ ወላጆች የምንደግፈው አይደለም ብለዋል።

የሚኒስቴሩ መመሪያ ከተሰማ በኋላ በተደጋጋሚ ከትምህርት ሚኒስቴር የበላይ አመራሮች ጋር ውይይት መቀጠሉን ተወካዮቹ አስታውሰዋል።

አንድ ወላጅ ለድሬቲዩብ በሰጡት አስተያየት መመሪያው ከወጣ በኋላ የትምህርት ሚኒስቴር ለሶስት ጊዜያት ያህል ት/ቤቶችን፣ አንድ ጊዜ ከወላጆች ጋር መመካከሩን፤ አሁንም ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጣ ኮምቴ ውይይት መቀጠሉን በአዎንታ እንደሚያዩት ጠቅሰው ከሚደረጉ ውይይቶች ሁሉንም ወገኖች ተጠቃሚ የሚያደርግ ውጤት እንደሚጠብቁ ተስፋቸውን ገልጸዋል።

“ምክክሩ ውጤት ባያስገኝስ?” ለሚለው ጥያቄ በአሁኑ ሰዓት አንዳንድ በውጪ ሀገር ለብዙ ዓመታት ቆይተው የተመለሱና በልዩ ልዩ የኢንቨስትመንትና የሙያ ዘርፎች ተሰማርተው የነበሩ ወላጆች ልጆቻቸውን ለማስተማር ሲሉ ተመልሰው ከሀገር ስለመውጣት እያሰቡ ነው። ይኸ ደግሞ እንደሀገር አይጠቅምም ካሉ በኋላ በምክክሩ ውጤት የማናገኝ ከሆነ በፍርድቤትም ቢሆን መብታችንን ለማስከበር መንቀሳቀሳችን አይቀርም ብለዋል።

ለአለመግባባቱ መንስኤ የሆነው መመሪያ ትምህርት ሚኒስቴር አለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ከተማሪዎቻቸው ቢያንስ 30 በመቶ የውጭ ሀገር ዜጋ ተማሪዎች ካልሆኑ አብዛኞቹ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤቶች ያንን መለያ ሊነጠቁና በሀገር ውስጥ እንዳሉት ሌሎች የግል ትምህርት ቤቶች ሊመደቡና የኢትዮጵያን ስርዓተ ትምህርት እንዲተገብሩ ይገደዳሉ ማለቱ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዓለም የቡና ገበያ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገለጠ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በቡና አቅርቦት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ስጋት...

አሜሪካ የኢራንን የጭነት መርከብን መያዟን አስታወቀች

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል ወደ ኢራን ወደቦች የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የዘጋችው...

“ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ቀይሮታል!” — ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

በ"ወቸው ጉድ" ፖድካስት ላይ እንግዳ ሆነው የቀረቡት ፕሮፌሰር ብርሃኑ...