ከበርካታ የነጠላ ዜማ ስራዎቿ ማግስት ‹‹እንደምንም›› የሚል መጠሪያ የሰጠችውን ቀዳሚ የአልበም ስራ ለሙዚቃ አፍቃሪያን ያደረሰችው ወጣቷ ድምጻዊት ዘቢባ ግርማ ከመሰንበቻ ፕሮግራም ጋር ቆይታ አድርጋለች፡፡
ቀዳሚ የአልበም ስራዋ ከፍተኛ ውጣውረድ የታለፈበት እና ተስፋ አስቆራጭ ፈተናዎች በጉዞ ውስጥ አጋጥመዋት እንደነበር ድምፃዊቷ በቆይታዋ አንስታለች፡፡
‹‹ምነው ባልሰራስ? ›› ብዬ የተበሳጨሁባቸውና የማይታለፉ የሚመስሉ ጊዜያት አጋጥመውኝ ነበር የምትለው ድምፃዊቷ በሂደት ግን የትዳር አጋሯን ጨምሮ ሌሎች ብርቱ ባለሙያዎች አቅም መሆናቸውን አልበሙን እውን ሊያደርገው እንደቻለ አንስታለች፡፡
ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1
