በአማራ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጨመረ

Date:

በ አማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ እና በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በኮሌራ ወረርሽኝ በርካታ ሰዎች እየተያዙ መሆኑን የክልሉ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች እና የጤና ሁኔታዎች ምላሽ አሰጣጥ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ እንደገለጹት ወረርሽኙ ከተከሰተበት ቀን ጀምሮ በየቀኑ የሚደርሰው የበሽተኛ ቁጥር እየጨመረ ነው፡፡ በተለይ በባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ በቀን ውስጥ በርካታ ሰዎች በበሽታው እየተጠቁ ነው ብለዋል።

አጣዳፊ ተቅማጥ እና ትውከት በማስከተል ለሞት የሚዳርገው በሽታው በክልሉ ከየካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ መከሰቱን አስረድተዋል ሲል አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ሲስተር ሰፊ ደርብ የኮሌራ የተበከለ ውኃ እና ምግብን በመጠቀም የሚከሰት ሲኾን ሰዎች በብዛት በሚሠባሠቡባቸው ቦታዎች በተለይም ንጹህ የመጠጥ ውኃ እና ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ በሌለበት አካባቢ በቀላሉ የሚተላለፍ በመሆኑ ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል።

በሽታውን ለመከላከል ከበሽተኛ ጋር ንክኪ ከተደረገ በኋላ እጅን በሳሙና መታጠብ፣ ውኃን በኬሚካል አክሞ እና አፍልቶ መጠቀም እንዲሁም የበሽታው ምልክቶች ከታዩ በአቅራቢያ ወደሚገኝ የጤና ተቋም በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት ያስፈልጋል ብለዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ዳውድ ኢብሳ ከምርጫው ራሳቸውን አገለሉ

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በኦሮሚያ...

ኢራን ከአሜሪካ ጋር ‹‹ሁሉን አቀፍ ስምምነት›› እንደምትፈልግ ገለጸች

ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት ለማቆም ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው...

የሪል እስቴት ዘርፍ ዘመናዊ የክፍያ ቴክኖሎጂን ለማስፋፋት አዲስ አጋርነት ፈጠረ

በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑት ድርጅቶች አንዱ...

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...