<<ናይጄሪያ በአፍሪካ ፍጹም ድሆችን በመያዝ ቀዳሚዋ ሆናለች>> የዓለም ባንክ

Date:

ናይጄሪያ በ ቦላ ቲኑቡ ስር ከፍተኛውን የድሆች ቁጥር ማስመዝገቧን የአለም ባንክ አስታወቀ

የአለም ባንክ በሪፖርቱ እንዳስታወቀው ከሰሃራ በታች ያሉ ሃገራት ከፍተኛውን የድሆች ቁጥር በመያዝ ከአናት የተቀመጡ ሲሆን ጥቂት ሃገራት ደግሞ ሰፊውን ድርሻ ወስደዋል ብሉዋል፡፡

ከአፍሪካ ሃገራት አንዱዋ የሆነችው ናይጄሪያ በቦላ ቲኑቡ እየተመራች 19 በመቶ ፍጹም ድሆችን በመያዝ ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡

ከናይጄሪያ በመቀጠል ፍጹም ድሆችን በመያዝ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በ14 በመቶ ስትከተል እንደ የ አለም ባንክ ሪፖርት ሃገራችን ኢትዮጵያ በ 9 በመቶ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡አራተኛውን ደረጃው ሱዳን በ 6 በመቶ ይዛለች፡፡

እንደአለም ባንክ ዘገባ በ2024 ሰራሁት ባለው ጥናት 80 በመቶ ወይንም 695 ሚሊየን ፍጹም ድሆች የሚገኙት ከሰሃራ በታች ባሉ ሃገራት እንደሆነ የገለጸ ሲሆን የደቡብ እሲያ ሃራት 8 በመቶውን ይይዛሉ፡፡

የተቀሩት ደግሞ 2 በመቶ ሰሜን ኤዢያ እና የፓስፊክ ሃገራት 5 በመቶ ደግሞ የመካከለኛው ምስራቅና የሰሜን አፍሪካ ሃገራት እንዲሁም 3 በመቶ ላቲን አሜሪካና የካረቢያን ሃገራት ይይዛሉ ዘገባው የ ወርልድ ባንክ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...

ትራምፕ ኢራን ላይ ያላቸው ትዕግሥት እየተሟጠጠ መሆኑን ተናገሩ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ጋር...