በአዲስ አበባ በአማካኝ ከ28 እስከ 30 ሺሕ የሚሆኑ ባለቤት አልባ ውሾች እንደሚገኙ ተነግሯል

Date:


ባለቤት አልባና በተለያዩ በሽታ የተጠቁ ውሾችን ለማስወገድ የሚያገለግለውን መድኃኒት ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት በግዢ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶአደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን አስታውቋል።

የትኞቹም ውሾች ባለቤት ሊኖራቸው እንደሚገባ የገለጹት የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ፤ ከዛ ባሻገር ግን አስፈላጊውን ክትባት መውሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም በአዲስ አበባ በአማካኝ ከ28 እስከ 30 ሺህ የሚደርሱ በጎዳና ላይ የሚኖሩ ወይም ባለቤት አልባ ውሾች እንደሚገኙ አንስተዋል።

ጎዳና ላይ የሚኖሩ ባለቤት አልባ ውሾችን በዘመቻ ክትባት የመስጠት፣ የማኮላሸትና እንዳይራቡ የማድረግ ሥራ እንደሚሰራ ገልጸዋል። በተለያየ ሁኔታ ለበሽታ የሚያጋልጡና የታመሙ ውሾች ካሉም ሕብረተሰቡ ላይ አደጋ እንዳያደርሱ ተቋሙ የማስወገድ ሥራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

እነዚህን ውሾች ለማስወገድ የሚያስፈልገው መድኃኒት እጥረት እንደነበረ ያነሱት ኮሚሽነሩ፤ በአሁኑ ወቅት ያሉትን ችግሮች በማስተካከል ከውጪ ወደሀገር ውስጥ በማስገባት በግዢ ሂደት ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

ከዚህ ቀደም በኮሊደር ልማቱ ምክንያት የልማት ተነሺዎች አብዛኞቹ ውሾቻቸውን ትተው ይሄዱ እንደነበረ የገለጹም ሲሆን፤ “መፍትሄ የሚያገኙበት ሁኔታ ይኖራል” ብለዋል።
በተጨማሪም በዚህ ዙሪያ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለመፍጠር ትኩረት ተደርጎ እንደሚሰራበት ገልጸዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የከተማ ግብርና መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ ስለሺ በቀለ በበኩላቸው፤ ከከተማ ውጪ ገጠር ላይም ቢሆን አንድ ሰው የራሱ የሆነ ውሻ ሲኖረው ውሻውን መንከባከብና ማኖር የሚገባው በቤቱ ውስጥ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

ይህም በአዲስ አበባ የከተማዋን ደንብና መመሪያ ተከትሎ እንደሚሄድ የገለጹ ሲሆን፤ ከዚህ በመነሳት የአዲስ አበባ ከተማ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን የሚሰራውን ሥራ ሚኒስቴሩ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በዚህም መሠረት ከባለቤት አልባ ውሾች ጋር በተያያዘ ያለው ችግር በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚቀረፍ ገልጸዋል።

(አሐዱ ሬዲዮ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...